እንኳን ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና እና ስፖርት ቢሮ በደህና መጡ
Addis Ababa City Administration Youth and Sports Bureau

Addis Ababa City Administration Youth and Sports Bureau
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በከተማው አስተዳደር ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 74/2014 የተቋቋመ ሲሆን፤ ከተማይቱ በወጣቶችና በስፖርት ዙሪያ የምትሰጣቸውን አገልግሎቶችና ከዚህ በተያያዘ የሚከናወኑ ተግባራትን የሚፈፅምበትና የሚያስፈፅምበት ስልጠንና ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
ቢሮው በዚህ አዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት ላይ ተመስርተው የሚሰጡ አገልግሎቶችና የሚከናወኑ ተግባራት፤ በአንድ በኩል በከተማችን የሚገኙ ወጣቶች በተናጠልም ሆነ በፍላጎትና ፍቃዳቸው ተደራጅተው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማስጠበቅ እንዲችሉ፤ በከተማዋ በተገነቡ የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ማግኘት፤ ካሉበት ወቅትና ከሚኖሩበት አከባቢ ነባራዊ ሁኔታ ጋር መራመድ የሚያስችል ግንዛቤ መጨበጥ እና ፍላጎትና ክፍተቶቻቸውን ያገናዘበ ስልጠና ማግኘት በአካልና አእምሮ እንዲዳብሩ፤ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ በሚፈጥራቸው የሥራ ዕድሎች ግንባር ቀደም ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና በየደረጃው ባሉ አደረጃጀቶች፣ በሲቪክ ማህበራትና መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የተሳታፊነትና የውሳኔ ሰጪነት ሚናቸው እንዲጎለብት የሚሰሩ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል የስፖርት ማበልጸጊያ ማዕከላትንና ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በየደረጃው በመገንባትና በማስፋፋት፣ የስፖርት ማህበራትን በማደራጀት በስፖርት ስልጠናና ውድድር በአካል ብቃት እንቅስቃሴና በስፖርት መዝናኛ የኅብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚነት የማስፋትና የማጠናከር፣ ተተኪ ስፖረተኞችን የማፍራትና ተወዳዳሪና ውጤታማ የማደረግ ስልጣንና ተግባር በአዋጁ ተሰጥቶታል፡፡
ይህንኑ መሠረት በማድረግ ቢሮው የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ ለመፈፀም አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀትና አሰራር በማጥናት የተገልጋዮችን ፍላጎትና እርካታቸውን ለማረጋገጥ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ እና የሚዛናዊ ውጤት ተኮር ስርዓት ጥናት ሰነዶችን በማዘጋጀት ወደ ትግበራ ተሸጋግሯል፡፡
የአንጋፋውን የመቻል ስፖርት ክለብ ታሪክ እና አሁን የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ለሀገራችን ስፖርት እያበረከተ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለአምባሳደሩ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም ስፖርተኞችን ፣ የክለቡን ሙዚየም እና ጂምናዚየም ጉብኝተዋል። አምባሳደር ቦስካን የመቻል ስፖርት ክለብን በመጎብኘቴ ደስታ ተስምቶኛል በቀጣይ ከመቻል ጋር አብሮ በስፖርቱ ዘርፍ ለመስራት የአዘርባጃን መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል።አዘርባጃን አምባሳደር ቦስካን
In 2017, our participant and beneficiary was youth; Sports and its culture made society and our competitive outcome is the athlete of nature.
Our centers will strengthen their capacity by expanding their facilities, strengthening associations, expanding movement and participation programs;
Transparency
Fairness
Community
Accountibility