የታዳጊ ስፓርተኞች የአመጋገብ ስርዓት ማሻሻል ለ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የታዳጊ ስፓርተኞች የአመጋገብ ስርዓት ማሻሻል ለስፓርት ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ

የታዳጊ ስፓርተኞች የአመጋገብ ስርዓት ማሻሻል ለስፓርት ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ

ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የጀመረው የአመጋገብ ስርዓት ማሻሻል እንቅስቃሴ ለስፓርት ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ።

በጃን ሜዳ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተካሄደው ምልከታ ላይ የዩኒሴፍ ኢትዮጵያ እና የቀጠናው ከፍተኛ ኃላፊዎችን ጨምሮ ታዳጊ ስፓርተኞች እና የቢሮ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል

በቢሮው ከዩኒሴፍ በተገኘ ድጋፍ የተስሩ ሥራዋች አስመልክቶ ለድርጅቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ገለጻ ያደረጉት የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ በማዕከሉ የተስራው ስራ ውጤታማ በመሆኑ ገቢ መፍጠር መቻሉን አስረድተዋል

የስፓርተኞች አመጋገብ በሳይንሳዊ ጥናት መደገፍ እንደ አገር የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ የገለጹት አቶ ጎሳዬ ከልምምድ በኋላ ምገባ ሥርዓትን በስፋት ለማስጀመር ያሉ የበጀት ውስስነት ለመቅረፍ በጋራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል

ጤናማ የአመጋገን ሥርዓት መዘርጋት ለታዳጊዋች እድገትንና ጤና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማበርከቱ ባሻገር በዝናባሌያቸው ለሚሰለጥኑ ስፓርተኞች ውጤታማ ለመሆን አመጋገባቸው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጽዋል

በማዕከላቱ በንብ ማነብ፣ በጎሮ አትክልት እና በዶሮ እርባታ የሚገኘው ምርት የስልጠናው ተሳታፊ ታዳጊዎች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰልጣኝ ቤተሰቦች ተጠቅሚ እየሆኑ እንደሚገኝ መገለጹ ይታወሳል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.