
ቢሮው የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ
ቢሮው የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ
ጥቅምት 21 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የሦስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
በውይይቱ ላይ የተገኙት አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ቢሮው በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት የወጣቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የከተማውን ሁለንተናዊ የስፖርት እድገት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
በከተማችን የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማቶች ለከተማው ወጣቶች የስራ እድል የፈጠሩ እንዲሁም የተከማዋን የስፖርት ማዘውተሪያ እጥረትን እየፈቱ መሆኑን የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል።
በመጀመሪያው ሩብ አመት ለከተማው ወጣቶች በተከታታይ በተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከ21 ሺህ በላይ ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩን የተናገሩት አቶ በላይ ከ62ሺህ በላይ ለሚሆኑ ታዳጊዎችም በ19 የስፖርት አይነት ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል።
በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ2ሚሊየን በላይ የከተማዋን ወጣቶች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በማሳተፍ በ14 የበጎ ፈቃድ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከ1.5 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ የቢሮ ሀላፊው ገልፀዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት አመት የሶስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን የቢሮው የእቅድ በጀት ግምማ እና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አበባየሁ በዝርዝር አቅርበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.