
ቋሚ ኮሚቴው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።
ቋሚ ኮሚቴው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀምን ገመገመ።
ጥቅምት 21 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ማህበራዊ ጉዳይ ቆሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርተን ገመገመ።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ለቆሚ ኮሚቴው ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የከተማውን ወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የስፖርት ልማት እቅዱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በዝግጅት ምዕራፍ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በከተማዋ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማቶች ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር እና የስፖርት ማዘውተሪያ ከማስፋፋት አኳያ ጥሩ እድል ይዞ መምጣቱን ያወሱት አቶ በላይ የከተማው ወጣቶች የልማቱ ዋና ባለቤት መሆናቸውን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቆሚ ቆሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት በወጣቶች እና በስፖርት ዘርፉ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
ቢሮው ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ ቦታን ከመስራት አኳያ ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ የሚሆን ስራን መስራቱን የተናገሩት ወ/ሮ ዘይነባ ተሞክሮውን በማስፋፋት ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት ቢሮው በሩብ ዓመቱ የሰራቸው ስራዎች ተዘዋውረው የተመለከተ ሲሆን የተሰሩ ስራዎችን አድንቀው በቀጣይ ሊስተካከሉ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች አመላክተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.