ቢሮው ለሜቄዶንያ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል 1ሚ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    2

ቢሮው ለሜቄዶንያ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል 1ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብ እና ምግብ ነክ ድጋፍ አደረገ

ቢሮው ለሜቄዶንያ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል 1ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብ እና ምግብ ነክ ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 25 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል 1ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብና ምግብ ነክ ድጋፍ አደረገ

የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ጨምሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የአዲስ አበባ ስፓርት ክለብ ደጋፊዎች እና በጎ ፍቃደኞች በክቡር ዶክተር ቢንያም በለጠ የተቋቋመውን በሜቄዶንያ ሰፊ ጎብኝት በማድረግ ከ1ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብ ነክ ድጋፍ አድርገዋል

ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ ይበቃል በሚል መርህ በሜቄዶያ እየተከናወነ የሚገኘው ለትውልድ መሻገር የሚችል በጎ ሥራ ማገዝ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት ነው ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ማዕከሉን በቢሮው ስር ያሉ ወጣቶችና ስፓርት ቤተሰቦች እንዲጎበኙ እንደሚደረግ ገልጸዋል

ማዕከሉ የበርካቶች ሕይወት እንዲስተካከል ከሕመም እንዲፈወሱና ከጉዳት እንዲያገግሙ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ያደነቁት አቶ በላይ በስሩ ያሉ ታካሚዎች በስፓርት ጤናቸውን እንዲጠብቁ እና ስፓርት እንዲዘወተር ለማድረግ በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል

በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ያሉ 44 ቅርንጫፎችን ሳይጨምር በአዲስ አበባ ብቻ 7500 ስዎችን በቀን ከ1.2ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እያደረገ የሚመግበውን ለሜቄዶንያ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ዳይፐር አልባሳት ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲደረግ አቶ በላይ ጥሪ አቅርበዋል

ቢሮው ለማዕከሉ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና የማእከሉ መስራች እና ሥራ አስኪጅ ቢንያም በለጠ በማዕከሉ እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ መመገብ እና መፀዳዳት የማይችሉ ዳይፐር ተጠቃሚ አልጋ ቁራኛ የሆኑትን ወገኖች ለማገዝ ሁሉም ሰው በሙያው እንዲያገለግል ጠይቀዋል

በጉብኝቱ የተሳተፉ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት በሰጡት አስተያየት በሜቄዶንያ እየተከናወነ የሚገኘው የበጎነት ስራ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልጸው ማዕከሉን ባላቸው አቅም ለማገዝ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል

ሜቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ጥቅምት 25 ቀን የወጣቶችና የስፓርት ቤተሰቦች ቀን ተብሎ መሰየሙን ማዕከሉ ይፋ አድርጓል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.