ቢሮው ከIYF ጋር የሁለትዮሽ የስምምነት ፊርማ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    1

ቢሮው ከIYF ጋር የሁለትዮሽ የስምምነት ፊርማ አካሄደ

ቢሮው ከIYF ጋር የሁለትዮሽ የስምምነት ፊርማ አካሄደ

ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ መቀመጫውን ኮርያ ካደረገ ዓለም አቀፈ የወጣቶች ፊሎሺፕ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የሁለትዮሽ የፊርማ ሥነ ስርዓት አካሄደ

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥበቡ በቀለ የከተማውን ወጣቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚሰሩ አካላት በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውሰው IYF

በቴኳንዶ፣የኮርያ ቋንቋ፣የበጎ ፍቃድ እና የማይንድሴት ስልጠና ለመስጠት ላሳየው መነሳሳት ምስጋና አቅርበዋል ።

የቃኘው ሻለቃን ገድል በማውሳት የኢትዮጵያና ኮርያ ከማህበራዊ ግንኙነት ባለፈ መስዋዕትነት የተከፈለበት ጠንካራ ግኑኝነት አላቸው ያሉት አቶ ጥበቡ የወጣቶች የስራ ተነሳሽነት ለመጨመር በስራ ፈጠራ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል በኮርያ በጎ ፍቃደኞች የሚሰጡ ስልጠናዎች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል

የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት ይህን በበኩላቸው ድርጅቱ ከቢሮ ጋር በነበረው ስምምነት በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን አስታውሰው አሁን በተደረገው ስምምነት

ለወጣቶች ነጻ የትምህርት ዕድ፣የኮርያ ቋንቋ ስልጠና ስፓርታዊ ስልጠና ጨምሮ በበጎ ፍቃድ ስራዎች እንደሚሳተፉ ገልጸዋል

ለወጣቶች የማይንድ ሴት ስልጠና በመስጠት ህብረተሰብን እንዲያገለግሉ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን የገለጹት የIYM ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ናም ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በመላው ኢትዮጵያ በመንቀሳቀስ ወጣቶች በስራ እንዲጠነክሩ ለማድረግ እየሰራ ያለውን በስፋት እንደሚሰራ ተናግረዋል

ወጣቶች በስፓርት አካላቸው እንዲዳብር እና አዕምሮዎቸው ንቁ እንዲሆኑ ግንዛቤ ለመፍጠር በስፋት እንደሚሰራ የገለጹት ዳይሬክተሩ ወጣቶችን ለማሰልጠን እና ከኮርያ አቻቸው ልምድ እንዲያገኙ ለማስቻል ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል

በስምምነቱ ከኮርያ፣ከቻይና ከሜክሲኮ የመጡ በጎ ፍቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁለትዮሽ ስምምነቱ የጎላ ሚና እንዳለው ተመልክቷል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.