
#የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴ_ለሁለንተናዊ_ብልፅግና
#የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴ_ለሁለንተናዊ_ብልፅግና
ከ500ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እሁድ ህዳር 1 ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ይካሄዳል። አቶ በላይ ደጀን።
ጥቅምት 29 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
ከ500ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፋበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም እሁድ ህዳር 1/2017ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን አሳውቀዋል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተመረጡ ቦታዎች እንደሚካሄድ ያሳወቁት አቶ በላይ ሁሉም የመዲናዋ ነዋሪዎች እንዲሳተፋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እንዲሁም ጤናማ እና አምራች ዜጋን በመፍጠር የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በመዲናዋ ህብረተሰቡ በሚኖርበት፣ በሚማርበት እና በሚሰራበት አከባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሞች ተቋማዊ በሆነ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን አቶ በላይ አሳውቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.