አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ሞሐ ለስላሳ መጠጦች የ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ሞሐ ለስላሳ መጠጦች የ4ሚሊዮን ስምምነት ተፈራረሙ

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ሞሐ ለስላሳ መጠጦች የ4ሚሊዮን ስምምነት ተፈራረሙ

ጥቅምት 30 2016 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አትሌቲክስ ፌድሬሽን እና ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክስዮን ማሕበር የ4ሚሊዮን የውል ስምምነት ፊርማ አካሄዱ

ዛሬ በጁፒተር ሆቴል በተካሄደው የሁሉትዮሽ የስምምነት ፊርማ ላይ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚዎች እና የሞሐ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በከተማዋ ሁለንተናዊ የአትሌቲክስ ስፖርት እድገት ላይ ድጋፍ የሚውል የ4 ሚሊዮን ብር ስፓንሰር ማድረጉን ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ በሁለትዮሽ የፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ባስተላለፉት መልዕክት ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪያል አክሲዮን ማህበር ለአገራችን ብሎም ለከተማችን ሁለንተናዊ የስፖርት ዕድገት እያበረከተ ለሚገኝው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበው ስምምነቱ ተተኪ እና ኤሊት ስፖርተኞችን በአትሌቲክስ ስፖርት ለማፍራት የሚደረገውን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ በእጅጉ ያግዛል ብለዋል

የከተማችንን ብሎም የሀገርን ስም በአለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የሚያስጠሩ አትሌቶችን ከማፍራት አኳያ ሞሐ ማህበራዊ ግዴታውን በመወጣት እንደ ባለቤት ሆኖ መሰረት ማስቀመጡን ያወሱት ፕሬዘዳንቱ ከፌዴሬሽኑ ከሞሐ ጋር በቅንጅት የሚሰራቸው ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል

የሞሐ ለስላሳ መጠጦች አክሲዮን ማሕበር ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ንጉስ ሰለሞን በበኩላቸው አክስዮን ማህበሩ ከ1989 ጀምሮ ላለፉት 28 ዓመታት ለሀገራችን ስፖርት እድገት እየሰራ የሚገኝ ድርጅት መሆኑን ገልጸው የ4 ሚሊዮን ብር ስምምነቱ ፌድሬሽኑ ለሚያከናውናቸው ውድሮችና የአትሌትክስ ፕሮጀክቶችን ለማስፋፋት የሚውል መሆኑን ገልፀዋል።

አትሌቴክስን መደገፍ ማህበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት ባሻገር ከአገር ጎን መቆም ነው ያሉት አቶ ሰለሞን ፌዴሬሽኑ ችግር ባጋጠመን ጊዜም ስያሜውን ሳይቀር ውድድር ማካሄዱን ጠቅሰው ሞሐ ለ50 ዓመታት ከአትሌቲክስ ስፓርት ጋር አብሮ ለመቆየት ያለውን ቁርጠኝነት አሳውቀዋል

ስምምነቱን የፈረሙት የፌድሬሽኑ ፕሬዘዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝና የሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዲስትሪያል አክሲዮን ማህበር ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ንጉስ ሰለሞን ሲሆኑ አትሌቲክስ ስፖርት ሁለንተናዊ እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመልክቷል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.