ከ500ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ከ500ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመዲናዋ ተካሄደ።

ከ500ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመዲናዋ ተካሄደ።

ህዳር 1 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ በ11ዱም ክፍለ ከተማ በተመረጡ አደባባዮች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል ከ500 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄደ።

በየካ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ብልጽግና ፓርቲ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለማጠናከር ስፓርት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል

ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግስት ለስፓርቱ ልዩ ትኩረት በመስጠት ወጣቱ ትውልድ በአካል እንዲዳብር በአእምሮ እንዲበለጽግ በመዲናዋ ከ1313 በላይ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የተናገሩት አቶ ሞገስ የብልፅግና ፓርቲ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶችን በመጠገን በሰው ተኮር ተግባር ያስመዘገባቸውን ስኬቶችን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ በ11 ዱም ክፍለ ከተሞች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ገለፀው ከ500ሺህ በላይ የህብተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ተናግረዋል።

የከተማዋን የስፖርት ልማት እቅድ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከለውጡ ወዲህ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን የገለጹት አቶ በላይ ወጣቱ የሚዝናናበት አካሉን የሚገነባበት ለሁሉም ምቹ የሆነ የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባታቸውን ገልጸዋል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመዲናዋ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ፣ ጤናማ እና አምራች ዜጋ ለማፍራት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተሰራ ስራ የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተቋማዊ እየሆነ መምጣቱን የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል ።

በአካል የዳበረ በአእምሮ የጎለበተ ትውልድ ለማፍራት እና ማህበራዊ ግንኙነት ለማጠናከር የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውን የገለፁት አቶ በላይ ህብረተሰቡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እራሱን ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እንዲከላከል አሳስበዋል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል በመዲናዋ በሚገኙ 11ዱም ክፍለ ከተሞች በድምቀት የተካሄደ ሲሆን የከተማው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.