የአልጄሪያ ወጣት ማህበር ልዑክ በወጣት ስብዕና...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    1

የአልጄሪያ ወጣት ማህበር ልዑክ በወጣት ስብዕና ማዕከል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጎበኘ ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአልጄሪያ ወጣት ማህበር ልዑክ በወጣት ስብዕና ማዕከል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጎበኘ

ሕዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከኢትዮጵያ አቻው ልምድ ልውውጥ ለማድረግ የመጣውን የአልጄሪያ ወጣት ማህበር አባላት ልዑክ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል የሚሰጡ አገልግሎቶች እና አጠቃላይ በወጣት ዘርፍ እንቅስቃሴ ዙሪያ ልምዱን አካፈለ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4ቁ 2 ወጣት ሰብእና መገንቢያ ማዕከል በተካሄደ የልምድ ልውውጥ የኢትዮጵያ ወጣት ማሕበር አመራሮች የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ተወካዮች፣ የአልጀሪያ የወጣት ማህበር ፕሬዘዳንትና አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ወጣት ማህበር አመራሮች እና አባላት በተገኙበት ተካሂዷል።

በወጣቶች የስብዕና መገንቢያ ማዕከል ለወጣቶች የሚሰጠው አገልግሎትና የወጣቶች ተሳትፎ ላይ ገለጻ ያደረጉት የወጣቶች ማብቃት ቡድን መሪ አቶ ሳሙኤል ምትኩ ቢሮ መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና ጨምሮ እውቀትና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል

በልምድ ልውውጥ በማዕከሉ ለወጣቶች የተፈጠሩ የሰራ እድሎችን፣የክበባት እንቅስቃሴ፣የቤተ መፅሀፍት አገልግሎት የሳይንስ ካፌውንና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.