
24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የከተማችንን ብሎም የአገራችንን መልካም ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንዲካሄድ የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። /አቶ በላይ ደጀን/
ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪሎ ሜትር ውድድር አስመልክቶ ከከተማው ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶች እና ከስፓርት ቤተሰቦች ጋር ውይይት አካሄደ።
ታላቁ የጎዳና ሩጫ በኢትዮጵያ በሁሉም የዕድሜ ክልል የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣አምባሳደሮች፣ እና ቱሪስቶች የሚያሳትፍበት ተናፋቂ የጎዳና ላይ ውድድር መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የከተማዋን ብሎም የአገራችንን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንዲካሄድ የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ለሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበል።
የዘንድሮ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በርካታ የኮሪደር ልማት ስራዎች በተጠናቀቁበት ጊዜ መደረጉ ለየት ያደርገዋል ያሉት አቶ በላይ ከተለያዩ አገሮች የሚመጡ የውጭ አገር ተወዳዳሪዎች የሚካፈሉበት እንደመሆኑ መጠን በፍጹም ሰላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች የላቀ ሚና እንዳለቸው አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በአለም የውድድር መድረክ ከፍ ያደረጉ አትሌቶች ደምቀው የሚታዩበት 24ኛው ታላቁ የጎዳና ሩጫ አብሮነት፣ ፍቅር እና ስፓርትን ማዕከል ያደረጉ መልዕክቶች የሚተላለፍበት መድረክ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በመዲናችን እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን አካተው እየተሰሩ መሆናቸውን ያወሱት አቶ በላይ
በሁለተኛው የኮሪደር ልማት 17 የስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚገነቡ ተናግረዋል።
የስፓርት መሰረታዊ ባህሪ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትን፣ አብሮነት እና ወድማማችነት ማስፈን መሆኑ የገለጹት ቢሮ ኃላፊው በ24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጠናከር የአትሌቲክስ ዓለም አቀፋዊ መርህ ተግባራዊ ለማድረግ ከአዘጋጁ አካል ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልፀዋል
የውይይቱ የተሳተፉ የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ለከተማችን ገጽታ ልዩ ትርጉም ያለው ታላቁ ሩጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ የተናገሩ ሲሆን ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እሁድ ህዳር 8/2017ዓ.ም መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ ይታወቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.