
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና የስፓርት ቤተሰቦች የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አስመልክቶ ውይይት ካደረጉ ቡኃላ ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና የስፓርት ቤተሰቦች የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አስመልክቶ ውይይት ካደረጉ ቡኃላ ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አወጡ
ህዳር 06 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
እኛ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ለ24ኛ ጊዜ በመዲናችን የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአማረ እና በደመቀ የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን መልካም ገፅታ መልኩ በሰላም እንዲከበር ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የጋራ ማድረጋችንን እናረጋግጣለን!!
1 የኢትዮጵያዉያን መለያና መገለጫ እየሆነ የመጣዉና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ የሆነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዘንድሮ ለ24ኛ ጊዜ ሲካሄድ በአማረ፣ በደመቀ እና ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን ለዓለም በሚያሳይ መልኩ በሰላም እንዲካሄድ የበኩላችን ድርሻ እንወጣለን
2 ዓለም አትሌቲክስ አስተዳዳሪ የ2017 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሩጫን የሌብል ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ሲል የሰጠው ዕውቅና በአንዳንድ ጽንፈኛ ሀይሎች ስሙ እንዳይጠለሽ ከፀጥታ አካላት በጋራ እንሰራለን
3 የዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት መቀመጫ የበርካታ ሁነቶች መከወኛ ፣ የአፍሪካውያን የፖለቲካ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት እያስመዘገበች ያለውን ስኬት ለአለም ለማስተዋወቅና የኮሪደር ልማቱን በባለቤትነት ለመጠበቅ ቃል እንገባለን
4 ብሔር፣ እምነት፣ የፖለቲካ አመለካከትና ጾታ ሳይለያየን በአገር ጉዳይ አንድ መሆናችንን ለአለም ለማሳየት በጋራ እንሰራለን
5 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለአብሮነት፣ ለአንድነት፣ ለወድማመችነት እና ለሀገር ግፅታ ግንባታ ለማዋል ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በጋራ እንስራለን፡፡
6 24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የከተማው ነዋሪ ሀላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን
7 ከተማ አስተዳደሩ በተለይ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማችን ታዳጊዎችና ወጣቶች እያበረከቱት ላለዉ ሁለንተናዊ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን
8 የስፖርት መገለጫ የሆኑትን ሰላም፣ ፍቅር፣አብሮነት፣ አንድነት እና ወድማማችነትን በ24ኛዉ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተግባር ለአለም ህዝብ አናሳያለን
9 መዲናችን አዲስ አበባ ህብረ ብሄራዊት የሰለም፣ የፍቅርና የብልፅግና ተምሳሌት መሆኖን በተግባር እንመሰክራለን
10 በ24ኛዉ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዉድድር ላይ በመገኘት አብሮነትን ሰላምን ፣አንድነትን፣ፍቅርን እና ወንድማማችነትን የሚገልፁ እና ልዩ ልዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ የከተማችንን መልካም ገፅታ እንገነባለን።
11 እኛ የአዲስ አበባ የስፓርት ቤተሰቦችና ወጣቶች ያለንን የስራ ተነሳሽነት በማስተባበር እና በማጠናከር ለስፓርት ኢንቨስትመንት ትልቅ ትርጉም ያለውን የ2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል 10ኪ.ሜ ሩጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻችንን እንወጣለን
በመጨረሻም ከላይ ያስቀመጥናቸውን የአቋም መግለጫዎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊና ተፈፃሚ ለማድረግ የምንሰራ ይሆናል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.