የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ደማቅ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ደማቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ደማቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

ሕዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከልደታ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ሕዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ አገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄደ

በብሪሞ ሜዳ በተካሄደው የብዙሐን አካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር፣ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ፣ የቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ፣ የልደታ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ደስታ ጨምሮ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች ወጣቶች፣ ታዳጊ ስፓርተኞች የማርሻል አርት እና የስፓርት ቤተስቦች እንዲሁም የህብረተስብ ክፍሎች በስፉት ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር ባሰሙት ንግግር ጠቅላይ ሚንስቴር ዶክተር አብይ አህመድ ታዳጊዎች ለትውልድ ቅድሚያ በመስጠት ለስሩት ሜዳ ምስጋና አቅርበው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናማ ማሕበረሰብ በመፍጠር አብሮነታችንን ከማወጁ ባሻገር ቤተሰባዊ ፍቅርን በመጨመር ረገድ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ዳዊት ትርፉ ስፓርት አንድነትን አብሮነትን እና ወድማማችነትን ከማጠናከር አኳያ ሰፊ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸው ከለውጡ ወዲህ የተሰሩ ወደ 1400 የሚጠጉ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ጤናማ በእዕምሮ የጎለመስ ትውልድ ለማፍራት ለምናደረግውን እንቅስቃሴ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው አካል ብቃት ስፓርት ለሰላም ለአንድነት ለፍቅር ያለውን ትልቅ አቅም ማሳየ ነው ያሉት አቶ ዳዊት የኢትዮጵያ ስፓርት ፓሊስ መሰረት በማድረግ ስፓርት ባህል እንዲሆን የምንሰራው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል

የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ደስታ በበኩላቸው መንግስት ለስፓርቱ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በርካታ ወጣቶች ተጠቃሚነት መሆናቸውን ገልጸው አንድነታችንን በማጠናከር ለአገራችን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በጋራ እንስራ ብለዋል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.