
24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ።
24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀመረ
ህዳር 8 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
24ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በቺካጎ ማራቶን የዓለማችን ፈጣኑን የማራቶን ሰዓት ያስመዘገበችው ኬንያዊቷ ሩት ቼፕንገቲች አስጀምራለች።
የኢፌድሪ ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ክብርት ሸዊት ሻንካ አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ እና አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ስፍራ ተገኝተዋል፡፡
የ2017 ሶፊ ማልት መነሻ እና መድረሻው መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ተጠናቀቀ
በዝግጅቱ ላይ ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ፣ከንቲባ አዳነች አቤቤ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ክብርት ሸዊት ሻንካ
የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ታዋቂ አትሌቶች አምባሳደሮች ጨምሮ 50ሺ ተሳታፊዎች እና ከ500 በላይ አትሌቶች ተሳትፈውበታል
ሴቶች ባደረጉት ውድድር
አሳየች አይቼው
የኔዋ ንብረት
ቦሰና ሙላት በመሆን አጠናቀዋል
በወንዶች
ቢኒያም መሐሪ
አዲሱ ነጋሽ
ይስማው ግሩም
በዚህ የፈጣን ማዕበል ሩጫ ከ10 ሺህ በላይ ሯጮች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ታዋቂ እና ታዳጊ አትሌቶች ተሳታፊ ናቸው፡፡
በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 10ኛ ለሚወጡት አትሌቶች የሜዳሊያ እና የገንዘብ ሽልማት የሚበረከት ሲሆን፣ ውድድሩን ላጠናቀቁት በሙሉ የሜዳሊያ ሽልማት ይሰጣል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.