
ዘወትር ሰኞ የምናደርገውን የዉይይት ፕሮግራም የሄድንበትን የ52 ሳምንታት ቆይታችንን ጥንካሬ እና ድክመት ለይተን ወደ ሌሎች ቢሮዎቻችን የምናስፋፋው ይሆናል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ዘወትር ሰኞ የምናደርገውን የዉይይት ፕሮግራም የሄድንበትን የ52 ሳምንታት ቆይታችንን ጥንካሬ እና ድክመት ለይተን ወደ ሌሎች ቢሮዎቻችን የምናስፋፋው ይሆናል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
“ወርቃማዋ ሰኞ” ብለን ዘወትር ሰኞ የምናደርገውን የዉይይት ፕሮግራም የሄድንበትን የ52 ሳምንታት ቆይታችንን ጥንካሬ እና ድክመት ለይተን ወደ ሌሎች ቢሮዎቻችን የምናስፋፋው ይሆናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በከንቲባ ጽ/ቤት እና በጊቢ ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጋር በመሆን “ወርቃማዋ ሰኞ” ብለን ዘወትር ሰኞ የምናደርገውን የዉይይት ፕሮግራም አንደኛ ዓመት ዛሬ ማለዳ አክብረናል ብለዋል።
እነሱ ጨለማው ሰኞ (Black Monday ) የሚሉትን እኛ ወርቃማው ሰኞ ብለን ላለፉት 52 ሳምንታት ከጥዋቱ 2 እስከ 3 ሰአት ባለዉ ጊዜ የከንቲባ ጽ/ቤትን ጨምሮ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የኮሙዩኒኬሽን እና የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በጋራ በመሆን በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን እና እየተመካከርን ሳምንቱ ሙሉ ወርቃማ እንዲሆንልን መልካም ምኞት ተለዋዉጠን አብረን ቡና ጠጥተን ስራችንን እንጀምራለን ሲሉ ገልጸዋል።
ይህንን የምናደርገዉ የበለጠ ለተገልጋዮች ቅርብ ለመሆን እና አገልግሎታችንን ለማሻሻል እርስ በእርሳችን የምንመካከርበት፣ የምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት እንዲሁም እንደ መሪ ታች ካሉ ሰራተኞቻችን ጋር ጭምር ማህበራዊ ህይወታችንን ከስራችን ጋር በማስተሳሰር ለመቀራረብ እና ሃሳብ ለመለዋወጥ ሲሆን በዚህ ሁኔታ 52 ሳምንታትን አሳልፈናል ሲሉ ተናግረዋል።
በዛሬዉ ፕሮግራማችን ደግሞ ዶ/ር ምህረት ደበበ ስለ ስራ እና ህይወት (work and life balance) ሚዛን መጠበቅ ትምህርት አካፍለውናል ብለዋል።
ፕሮግራሙ በከንቲባ ጽ/ቤት ይጀምር እንጂ ወደ ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት እና መስሪያ ቤቶች የሚሰፋ ሲሆን እስከ አሁን የሄድንበትን የ52 ሳምንታት ቆይታችንን ጥንካሬ እና ድክመት ለይተን ወደ ሌሎች ቢሮዎቻችን የምናስፋፋው ይሆናል ሲሉም አመለክተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.