ቢሮው ከIYF በመተባበር ያዘጋጀው የማይንድ ሴት...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    1

ቢሮው ከIYF በመተባበር ያዘጋጀው የማይንድ ሴት ስልጠና መሰጠት ጀመረ ሕዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

ቢሮው ከIYF በመተባበር ያዘጋጀው የማይንድ ሴት ስልጠና መሰጠት ጀመረ

ሕዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዓለም አቀፉ ወጣቶች ፊሎሺፕ/አይ.ዋይ.ኤፍ/ እና ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የማይንድ ሴት ስልጠና መሰጠት ጀመረ

መቀመጫውን ኮርያ ካደረገው ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የተቀየረ የወጣቶች የስራ ባህል ለብልጽግና በሚል መሪ ቃል በተሰጠው የማይንድ ሴት ስልጠና ላይ ከ1500 በላይ ወጣቶች ተሳትፈዋል

ለስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሃና በተለያዩ የስራ መስኮች ወጣቶች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸው የነገ ሃገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶች ባገኙት ስልጠና ራሳቸውን እና አገር ለመለወጥ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል

ኢትዮጵያና ኮርያ ከማህበራዊ ግንኙነት ባለፈ በደም የተሳሰረ የወንድማማችነት ግኑኝነት እንዳላቸው ያስታወሱት አቶ መክብብ የአባቶቻን ታሪክ ማስቀጠል የወጣቱ አ,ደራ እንደመሆኑ መጠን ለተተኪው ትውልድ የበለጸገች አገርን ለማሻገር ከኮሪያውያን በጎ ፍቃደኞች የአገኘነውን የስራ ልምድና የእውቀት ክህሎት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ደሊል በበኩላቸው ከቢሮ ጋር በመቀናጀት በስራ ፈጠራ ወጣቱን ለማነጽ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸውየተጀመረውን የልማት ጉዞ ዳር ለማድረስ ወጣቶች በስልጠናው ያገኙትን ልምድ ወደ ስራ በመቀየር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል

ቢሮው በቅርቡ ከአይ.ዋይ.ኤፍ ጋር

የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁለትዮሽ የስምምነት ፊርማ ማድረጉን ያስታወሱት የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት ይሁኔ ወጣቶች እምቅ አቅማቸውን በመጠቀም መስራት የሚችሉት ነገር ላይ ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ የሚሰጠው ስልጠና በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚካሄድ ገልጸዋል

ኢትዮጵያ ለኮርያ ዜጎች በጀግንነት በመታገል ያደረገችውን ውለታ በማውሳት ልዩ ክብር እንዳላቸው የገለጹት የማይድን ሴት ስልጠናውን የሰጡት የIYF አሰልጣኝ ዶክተር ሙ ወጣቶች

አወንታዊ አስተሳሰብ እና ከጥበበኛ ጋር በመዋል ሕይወታቸውን መለወጥ እንደሚችሉ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል

ራስህን በመገንባት፣በህይወታችሁ መድረስ የምትፈልጉት ነገር ላይ ለመድረስ እና ለማሰካት የምትፈልጉት ነገር በትምህርት፣ በስራና በፍቅር ማሳካት ትችላላችሁ ያሉት ዶክተር ሙ

በስራ ፈጠራ መንገዶች ተግዳሮቶችን እንዴት ማለፍ እንደሚቻል የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የተለያዩ ምሳሌዎችን በመጥቀስ ሰፊ ማብራርያ ሰጥቷል

ቢሮው በንቃተ ህሊና ላይ ለወጣቶች የሚሰጠው ስልጠናው በአስሩም ክፍለ ከተሞች እንደሚካሄድ የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር :- https://twitter.com/SportYout79296

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZMYR8WTs8/

👍👍👍 ኢሜል addissport2013@gmail.com


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.