ቢሮው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ቢሮው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ የፓናል ውይይት ከወጣቶች እና ከስፖርት ቤተሰባች ጋር አካሄደ።

ቢሮው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ ከተማ አቀፍ የፓናል ውይይት ከወጣቶች እና ከስፖርት ቤተሰባች ጋር አካሄደ።

ህዳር 13 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

"ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት"በሚል መሪ ቃል 19ኛዉን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ቀንን በማስመልከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦቻ ጋር የፖናል ውይይት አካሄደ።

የኢፌድሪ ሕገ መንግስት የጸደቀበት ሕዳር 29 ቀን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሚል ስያሜ ሕበረ ብሔራዊ አንድነት በሚያጠናክር መልኩ ላለፉት 19 ዓመታት ሲከበር መቆየቱን ያስታወሱት የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር ቀኑ በእኛ ኢትዮጵያዊን ዘንድ ትልቅ ሥፍራና ትርጉም ያለው የአገራዊ እሴት፣ የአብሮነታችን ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የእኩልነት፣ የዲሞክራሲ እና የኢኮኖሚ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ የሰጠ ነው ያሉት ወ/ሮ ዘይነባ ከተማ አስተዳደሩ በሕዝቦች መካከል የእርስ በእርስ ትስስርን በማጠናከር መልካም እሴቶቻቸውን እንዲያዳብሩ ለማድረግ የሚሰራው ስራ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ስናከብር በህዝቦች መካከል መልካም ግንኙነትን በመፍጠር ብሎም አብሮነትን አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችንን በመተግበር ሊሆን ይገባል ብለዋል።

19ኛውን የብሔር ብሔረሰባች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከ75 በላይ ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች የፖናል ውይይት ማካሄዳቸውን የተናገሩት አቶ በላይ ከግማሽ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን የተሳተፋበት የብዙሀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዶል ብለዋል።

በአዲስ አበባ እየተከናወነ በሚገኘው የመንገድ ኮሪደር ልማት ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚ መሆናቸውን ያወሱት የቢሮ ሀላፊው አዲስ አበባ የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ዋና ከተማ እንደመሆኗ መጠን በእኩልነትና በውይይት የሚያምን ወጣት ለመገንባት የምንሰራው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል

ለፖናል ውይይት መነሻ ሰነድ ለወጣቶቹ የቀረበ ሲሆን አቶ መክብብ ወልደ ሀና የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ወጣቶችን አወያይተዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+15

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

174Dawit Dave፤ Waaqkenee Dhuguma Saadeeta እና 172 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.