
የተቀየረ የወጣቶች የስራ ባህል ለብልጽግና በሚል መሪ ቃል የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጠ ሕዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የተቀየረ የወጣቶች የስራ ባህል ለብልጽግና በሚል መሪ ቃል የማይንድ ሴት ስልጠና ተሰጠ
ሕዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በምሕጻረ ቃል IYF ከዓለም አቀፉ ወጣቶች ፊሎሺፕ እና ከቦሌ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር የተቀየረ የወጣቶች የስራ ባህል ለብልጽግና በሚል መሪ ቃል የማይንድ ሴት ስልጠና ሰጠ
መቀመጫውን ኮርያ ካደረገው ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተሰጠው የማይንድ ሴት ስልጠና ላይ ከ1500 በላይ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ተሳትፈዋል
ስልጠናው የወጣቶች በአስተሳሰብ በመቀየር ራሳቸውንና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ ለማስቻል ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ያሉትየቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አሰፋ ኢትዮጵያ ባላት ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥርና ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት ወደ ብልጽግናዋ እንድትሸጋገር የሚያስችላት ነው ብለዋል
ቢሮው በቅርቡ ከአይ.ዋይ.ኤፍ ጋር
የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁለትዮሽ የስምምነት ፊርማ ማድረጉን ያስታወሱት የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት ይሁኔ ወጣቶች እምቅ አቅማቸውን በመጠቀም መስራት የሚችሉት ነገር ላይ ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ የሚሰጠው ስልጠና በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚካሄድ አጽንኦት ሰጥተዋል
የIYF አሰልጣኝ ራስህን መገንባት፣ የህይወታ መርህ ትምህርትና ጥበብ ስራና የስራ ፍቅርን ማሳደግ ላይ ከአገር እድገት ጋር በማገናኘት ሰፊ ማብራርያ ሰጥቷል
ቢሮው በንቃተ ህሊና ላይ ለወጣቶች የሚሰጠው ስልጠናው በአስሩም ክፍለ ከተሞች እንደሚካሄድ የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር :- https://twitter.com/SportYout79296
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZMYR8WTs8/
ኢሜል addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
62Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 60 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.