
5ኛ አመት የብልፅግና ፖርቲ የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ300ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
5ኛ አመት የብልፅግና ፖርቲ የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ300ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።
ሕዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል 5ኛ አመት የብልፅግና ፖርቲ የምሰረታ በዓል ምክንተያት በማድረግ ከ300ሺህ በላይ የህብረሰብ ክፍሎች የተሳተፋበት የብዙሃን የካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዳዋ ሙዚየም አከባቢ ተካሄደ።
በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የብልፅና ፖርቲ የአዲስ አበባ ቅርጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀንን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች በስፋት ተሳትፈውበታል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባሰሙት ንግግር አዲስ አበባን እንደ ስሞ ውብ አዲስ እናደርጋለን ብለን የገባነውን ቃል ከመላው የከተማችን ህዝቦች ጋር በጋራ በመስራት ለነዋሪዎቿ የምትመች እና የብልፅግና ተምሳሌት የሆነች ከተማን መፍጠር ችለናል ብለዋል።
በአእምሮ እና በአካል ብቃት የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ህብረሰቡ በሚኖርበት፣ በሚሰራበት እና በሚማርበት አከባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያካሂድበት ከ1300 በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ስፓርታዊ እንቅስቃሴ ጨምሮ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸው ብልጽግና ፓርቲ በአስተሳሰብ የላቀ በአካሉ የጠነከረ ትውልድ ለማፍራት እየሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት ምስረታ ምክንያት በማድረግ ቢሮው በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ወጣቶችና የስፓርት ቤተሰቦች አዲስ አበባን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
220Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 218 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.