የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት 17ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ህዳር 14 /2017ዓ.ም አካሂዷል።

በጥቅላላ ጉባኤው የተገኙት አቶ ረታ ብርሀኑ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚና የስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ስፖርት ፍቅርን እና አንድነትን መሰረት አድርጎ በወንድማማችነት እና እትማማችነት መንፈስ ለሀገር እድገት መሰረት የሆነ ዘርፈ ብዙ መስክ ነው ያሉ ሲሆን ስፖርት ያለ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና ያለጠንካራ መሪ የትም ስላማይደርስ የስፖርት ምክር ቤቶች ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ብርሀኑ አክለውም ክፍለ ከተማችን በርካታ ስፖርተኞችን ያበረከተ እና እያበረከተ ያለ እንዲሁም እምቅ ፀጋዎች እና መልክአ ምድር የያዘ በመሆኑ በጋራ ጸጋዎቻችንን መጠቀም መቻል ይኖርብናል ብለዋል፡፡

የስፖርት ምክር ቤቶ ምክትል ሰብሳቢ የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት ስፖርት ለሀገራችን ኢትዬጵያ ትልቅ ትርጉም ያለው በአለም ደረጃ የጥቁር ህዝብ አርማ አድረጎ ያስተዋወቀን ትልቅ ዘርፍ በመሆኑ በትኩረት ልንሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ በ2016 በጀት አመት በስፖርት ምክር ቤቱ በአዋጆች እና መመሪያዎች ዙሪያ ለስፖርት ቤተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር መቻሉ፣የህዝብ ተሳትፎ መድረኮች በማዘጋጀት የማህበረሰብ ስፖርት እንቅስቃሴዎች እና ፌስቲቫሎችን እንዲሁም የስፖርት ለሁሉም ፕሮግራሞች በማዘጋጀት ከእቅድ በላይ የህብረተሰብ ክፍል ማሳተፍ መቻሉ አቶ ዩሐንስ ስዩም አብራርተዋል።

የስፖርት ምክር ቤቱ የ16ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ የተጀመረ ሲሆን በ2016 በጀት አመት በስፖርት ምክር ቤቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ቀርበዋል፡፡

በተጨማሪም የስፖርት ማህበራት የማደራጀት እንዲሁም ክትትል እና ድጋፍ የማድረግ ስራ እና የህብረተሰብ ክፍሎችን እና የስፖርት ማህበራትን በማስተባበር ገቢ የማሰባሰብ እና የፋይናንስ አቅም የማሳደግ ስራም ተሰርቷል፡፡

በቀጣይም በ2017 በጀት አመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት እንደታቀደ እና የ2016 አፈፃፀምን መሰረት ያደረጉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተገልፃል፡፡

በመጨረሻም የስፖርት ምክር ቤቱ የ 2017 በጀት እቅድ የቀረበ ሲሆን ከተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶች የሚገኙ ገቢዎች እቅድ እና ለተለያዩ የስፖርት ውድድሮች እና ኩነቶች የሚስፈልግ በጀት ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን በሙሉ ድምፅም ጸድቋል፡፡

መረጃው የየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው

+3

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

152Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 150 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.