ቢሮው 9.1 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ሙሉ እድ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    1

ቢሮው 9.1 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ሙሉ እድሳት ያደረገላቸውን የአቅመ ደካማ ቤቶችን አስመረቀ

ቢሮው 9.1 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ሙሉ እድሳት ያደረገላቸውን የአቅመ ደካማ ቤቶችን አስመረቀ

ሕዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የከተማው ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦችን በማስተባበር በበጋ በጎ ፍቃድ በቦሌ ክፍለ ከተማ ያሳደሳቸውን 10 የአቅመ ደካማ ቤቶች አስመረቀ

የአቅመ ደካሞችን ኑሮ በማሻሻል የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሰው ተኮር ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኝ የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን የከተማችን ወጣቶችና የስፓርት ቤተሰቦች በማስተባበር የሚሰሩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥል ገልጸዋል

9.1ሚልዮን ብር የፈጀው የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ሲሰራ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የቅርብ ክትትል መደረጉ የገለጹት አቶ በላይ ቢሮው ውንድማማችነት እህትማማችነት ጎልቶ የሚታይበት የበጎ ስራ ተግባር በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል

የከተማውን ትልቅ ቁጥር እና አምራች ኃይል በመያዝ እየተከናውኑ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆኑን ያወሱት አቶ በላይ ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ በሃሳባቸው በጉልበታቸው እና በገንዘባቸው ላገዙ ወጣቶችና የስፓርት ቤተስቦች ምስጋና አቅርበዋል።

አቶ ይመር ከበደ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር በበኩላቸው የከተማውን የቆየ ችግር ለመፍታት በ2017 በጀት ዓመት 2700 በላይ ቤቶች መሰራታቸውን ገልጸው ከተማን ለመገንባት እየተከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል

በበጋ በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር ቢሮው ሙሉ እድሳት ያደረገላቸው ቤቶች ለነዋሪው ትልቅ እፎይታ የሰጠ መሆኑን የገለጹት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍጹም ኃይሌ እድሳት የተደረገላቸው ቤቶች መፀዳጃና የንፅህና መጠበቂያ ክፍሎች ጨምሮ ኪችን እንዳላቸው አስረድተዋል

በዛሬው ዕለት የመኖሪያ ቤታቸው ዕድሳት ተጠናቆ ቤታቸውን የተረከቡ ነዋሪዎች ላለፉት ዓመታት ለኑሮ ምቹ ባልሆነ ሒደት ውስጥ ያለፉ መሆናቸው ገልጸው ቢሮው ላደረገላቸው ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል

በክረምት በጎ ፈቃድ የከተማውን ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦችን በማስተባበር የተጠገኑ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ርክክብ ሲደረግ የማዕድ ማጋራት መከናወኑ ተመልክቷል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+9

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

148Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 146 ሌሎች

14

5

ይውደዱ

አስተያየት

ያጋሩ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.