
ቢሮው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ አስራር ግምገማ አካሄደ ሕዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ቢሮው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ አስራር ግምገማ አካሄደ
ሕዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የሴክተር ተቋማት ቅንጅት ትብብር ትግበራ አሰራር አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
ከተቋማት ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ውጤታማ ለማድረግ ወቅቱን የጠበቀ ውይይት ማድረግ ወሳኝ መሆኑን ያወሱት የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መቅደስ አዱኛ በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሴክተር የወጣቱን ጉዳይ አብይ አጀንዳ በማድረግ የሰሩት ስራ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል
በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ የተሰሩ ሥራዎች ላይ ገለጻ ያደረጉት መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልሐሚድ ድሌቦ የሚያጋጥሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በቅንጅት መሰራቱን አመላክተዋል
ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ ቢሮው ከ16 ተቋማት ትስስር ማድረጉን ያስታወሱት አቶ አብዱልሐሚድ በቀጣይ የተግባር ምዕራፍ የወጣቶች ማህበራዊ አኪኖሚያዊ እና በፓለቲካው ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሴክተሮች እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ አጠናከረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል
ቢሮው በቅንጅታዊ አስራር ፋይዳ እና አጠቃላይ ዓላማ ላይ ውይይት ባካሄደበት ወቅት ስምምነቱን የፈረሙ ተቋማት መገኘታቸው ተመልክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
71Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 69 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.