ዘመናዊ የስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳ ግንባታ ለማስጀ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

ዘመናዊ የስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳ ግንባታ ለማስጀመር መሠረተ ድንጋይ ተጣለ

ዘመናዊ የስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳ ግንባታ ለማስጀመር መሠረተ ድንጋይ ተጣለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በመሪ ሎቄ ደረጃውን የጠበቀ 3በ1 የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድጋይ ተቀመጠ

ወጣቱ ትውልድ ትርፍ ጊዜውን አልባሌ ቦታ እንዳያሳልፍና ፍላጎቱን መሰረት ያደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን እንደ ከተማ አስተዳደርም ሀገር ተረካቢ ወጣት ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል

በባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት ውስጥ በተለይ አመራሩ ሞዴል ሆኖ የስፖርት ማዘወተሪያዎችና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ግንባታዎች በአብዛኛው ወጣቱ ላይ ትኩረት አድርገው መሰራታቸውን አቶ በላይ ገልጸዋል

አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብና ማራኪ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ እንድትሆን እየተሠራ ያለው ተግባር ባለሃብቱም ተሳትፎ እንዲያደርግ አቶ በላይ ጥሪ አቅርበዋል

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው እህፃናት በአካልና በአእምሮ የዳበሩ እንዲሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ቦታ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው ያለን አመራሮችና የማህበረሰብ ክፍሎች በቅንጅትና መስራት ይገባናል ብለዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+3

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

165Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 163 ሌሎች

15

8

ይውደዱ

አስተያየት

ያጋሩ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.