
በወጣት ማዕከላት የሚካሄደው ሪፎርም የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል ተገለጸ
በወጣት ማዕከላት የሚካሄደው ሪፎርም የሚነሱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እንደሚያስችል ተገለጸ
ሕዳር 19 ቀን 2017 ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ በወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት በዘርፍ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ባለፉት አራት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ
ለዝግጅቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሃና ወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ለወጣቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው የወጣቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል
የወጣቶች ማብቃት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ንብረት ይሁኔ በበኩላቸው ባለፉት አራት ወራት በዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት ላይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት የተሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት ለፈጸም ያደረጉት እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል
በመድረኩ የማዕከላቱን አገልግሎት አሰጣጥ የተመዘገቡ ጥንካሬ እና የታዩ ክፍተቶች ሰፊ ዉዉይት ተደርጎ መፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጧል
አቶ መክብብ ወልደሃና በሰጡት የስራ አቅጣጫ የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በወጣት ስብዕና ማዕከላት የሪፎርም ስራ የግንዛቤ ንቅናቄ ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተው ማዕከላትን በገቢ ምንጭ ለማጠናከር ጣልቃ ገብነት እና የሰው ኃይል ችግርን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
109Seyoum Wolde፤ Mes Ethio እና 107 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.