
ከ17ሺህ በላይ ታዳጊዎች የሚሳተፋበት የበጋ የታዳጊዎች የስፖርት ስልጠና መርሀ ግብር ተጀመረ።
ከ17ሺህ በላይ ታዳጊዎች የሚሳተፋበት የበጋ የታዳጊዎች የስፖርት ስልጠና መርሀ ግብር ተጀመረ።
ህዳር 21 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የታዳጊዎች የስፖርት ስልጣና መርሀ ግብርን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፋ በዘንድሮው የበጋ የታዳጊዎች የስፖርት ስልጠና ከ17ሺህ በላይ ታዳጊዎች ይሳተፋሉ ብለዋል።
በ20 የስፖርት አይነት በ11ዱም ክፍለ ከተማ በ383 የስልጠና ጣቢያዎች የስፖርት ስልጠናው እንደሚሰጥ አቶ ዳዊት ተናግረዋል።
የታዳጊ ወጣቶች ስልጠናን ዘመናዊ እና አለም አቀፍ የስልጠና መርህን በተከተለ መልኩ በማካሄድ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት በማፍራት የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን የስፖርት ትንሳኤ ለማሳካት ቢሮው ለታዳጊ ወጣቶች ስልጠና መርሀ ግብር ልዩ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ም/ቢሮ ሀላፊው አሳውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በ2016ዓ.ም የክረምት የታዳጊዎች የስፖርት ስልጠና ከ61ሺህ በላይ ስልጣኞችን በ20 የስፖርት አይነት ያሰለጠነ ሲሆን ስልጠናው እንዲሳካ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የስልጠና ጣቢያዎች፣ ክፍለ ከተሞች፣ አሰልጣኞች እና የስፖርት ባለሙያውች እውቅና ተሰጥቷል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
115You፤ Engdawork Daniel፤ Dawit Dave እና 112 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.