የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የብዙሃን...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በወዳጅነት ፖርክ ተካሄደ።

የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በወዳጅነት ፖርክ ተካሄደ።

ህዳር 22 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ከተማ የስነ-ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በአለም ለ21ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ደማቅ የብዙሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በወዳጅነት ፖርክ አካሄደ።

ወጣቶችን ያማከለ የፀረ ሙስና ትግል የነገን ስብዕናን ይገነባል በሚል መሪ ቃል በተካሄደ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ወጣቶች የማይተካ ሚና ያላቸው በመሆኑ በፀረ ሙስና ትግሉ የበኩላቸው አስተዋፅኦ እንዲወጡ አሳስበዋል።

ወጣቶች የእርስ በእርስ ትስስራቸውን በማጠናከር በአቋራጭ ከመክበር ይልቅ ሰርቶ የመለወጥ ባህልን ሊያዳብሩ ይገባል ያሉት አቶ በላይ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ህብረተሰቡ በሚማሩበት፣ በሚሰሩበት፣ በሚኖርሩበት የሚማካሄዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀማር ረዲ በበኩላቸው ጤናማ፣ ብርቱ፣ንቁ፣ ጀግና ዜጋ ማፍራት ከተቻለ አገርን ማበልጸግ ይቻላል ብለዋል።

ሙስናን ለመግታት እና በአገር ግንባት ውስጥ የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የገለፁት ኮሚሽነር ጀማል ወጣቶች በከተማቸው ብሎም በሀገራቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

ዛሬ በወዳጅነት ፓርክ በድምቀት በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ10ሺህ በላይ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና የስፓርት ቤተሰቦች ተሳትፈውበታል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+12

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

194Engdawork Daniel፤ Dawit Dave እና 192 ሌሎች

19

135

ይውደዱ

አስተያየት

ያጋሩ

ተጨማሪ አስተያየቶችን ይመልከቱ

 

Mite Haile


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.