
ቢሮው ከተማ አቀፍ የሦስት ወራት የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ
ቢሮው ከተማ አቀፍ የሦስት ወራት የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ
ህዳር 23 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የከተማ አቀፍ የ2017 የ3 ወር የስራ እድል ፈጠራ ንቅናቄ አስተሳሰብ ቀረጻ እና የሌማት ቱሩፋት እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ
በውይይት መድረኩ ላይ የቢሮ አመራሮች ጨምሮ የሁሉም ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎችየአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ወጣቶች ሊግ አመራሮች የወጣት ማህበር አመራሮች የማዕከል የወጣት ዘርፍ ባለሙያዎች እና የወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባሰሙት ንግግር ያሉ ጸጋዎች በመጠቀም ስራ ፈላጊ ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የንቅናቄ እና የማይንድ ሴት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አስታውሰው በቀጣይ ሦስት ወራት የሚከናወነው ወጣቶችን የመለየት የመመዝገብና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ አሳስበዋል
ከተማ አስተዳደሩ ከ150ሺ በላይ ወጣቶች በቋሚ የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የታቀደው እቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ያወሱት አቶ በላይ ውጤታማ የሆነው ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ስራ ወጣቱ ጠባቂ እንዳይሆን አስችሎታል ብለዋል
የወጣቶችና ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀጣይ ሦስት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ገለጻ ያደረጉት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሃና ከብሎክ እስከ ማዕከል በሚሰሩ ስራዎች የአገሪቱን ለውጥ መነሻ በማደረግ ባሉ አስቻይ ሁኔታዎች ጨምሮ በኢኮኖሚ ሪፎርም ዲጂታል ሪፎርም እና አገር በቀል ፈጠራዎች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል
የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ፕሬዘዳንት መለስ አባተ በበኩላቸው ወጣቱን በፖለቲካዊ ፣ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው ከተማ አስተዳደሩ ያቀደውን እቅድ ለማስካት በአስተሳሰብ ቀረጻ እና ንቅናቄ ላይ በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪያቸውን አቅርበዋል
ቢሮ ኃላፊው በሰጡት የስራ አቅጣጫ የስራ እድል ፈጠራና የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ እቅዱን ከግብ ለማድረስ ወጣቶችን በተደራጀ መንገድ መመዝገብ፣ ግንዛቤ በመፈጠር፣ወደ ስልጠና በማስገባትና መስሪያ ቦታ እና ብድር ማመቻቸ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
141Gossaye Alemayehu፤ Yewubdar Getnet እና 139 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.