14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    1

14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ

14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር እና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀመረ

ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አዘጋጅነት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት የሚካሄደው 14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ተከፈተ

ዛሬ በአልማዝዬ ሜዳ በተካሄደው የመክፈቻ ዝግጅት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የከተማ እና የክፍለ ከተማ አመራሮች ጨምሮ ከአስረ አንዱም ክፍለ የተውጣጡ ከ10ሺ በላይ የስፓርት ልዑካን ተሳታፊዎች ተገኝተዋል

ውድድርና ፌስቲቫሉ በከተማችን ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች እውቅና ከመስጠቱ ባሻገር ማህበራዊ ፣ኢከኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ፓለቲካዊ ጥቅማቸውን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በሰባት የጉዳት አይነት የሚካሄደው ውድድር አካል ጉዳተኞች በስፓርት ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ከተማ አስተዳደሩን እና አገርን የሚወክሉ ምርጥ ስፓርተኞችን ለማፍራት ያስችላል ብለዋል

የአካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው ውድድና ፌስቲቫል ሕበረብሔራዊ ወንድማማችነት ከማሳየቱ ባሻገር የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ሚና የሚያጎላ ነው ያሉት አቶ በላይ አካል ጉዳተኛ ወገኖቻችንን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ክብርና ማህበራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪያቸውን አቅርበዋል

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ገነት ቅጣው በበኩላቸው የአካል ጉደተኞች ቀን በሀገራችን ለ32 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ እየተካሄደ እንደሚገኘው ገልጸው 14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው የስፖርት ፌሰቲቫል ውድድር ሁለንተናዊ የስፓርት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል

ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች የስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ክፍለ ከተማው ለማሰናዳት በመመረጡ የተሰማቸውን ደስታ የገለጹት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ ውድድሩ አካል ጉዳተኞችን በማሳተፍና ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በአገር አቀፍ ውድድር ከተማችን የሚወክሉ ተተኪ ስፓርተኞችን ለማፍራት እንደሚያስችል ገልጸዋል

ስፓርቱ በከተማችን ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች እውቅና ከመስጠቱ ባሻገር ማህበራዊ ኢከኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ፓለቲካዊ ጥቅማቸውን እንደሚያረጋግጥ የገለጹት የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማህበር ፕሬዘዳንት ዶክተር ወይንሸት ግርማ ፕሮግራሙ ላዘጋጁት አካላት እና ለተሳታፊ ስፓርተኞች ምስጋና አቅርበዋል

የአካል ጉዳተኞች የስፖርት ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 14ኛው የአካል ጉተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፓርታዊ ውድድር ከህዳር 24 እስከ ታሕሳስ 6 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ዛሬ በመክፈቻው በተካሄደ የእግር ጉዳት የገመድ ጉተታ ውድድር ቦሌ ቂርቆስ ክፍለ ከተማን ሁለት ለባዶ አሸንፏል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍 you tube https://www.youtube.com/channel/UC0CARW3IdFaPlZ980VITn5Q

👍👍👍ትዊተር :- https://twitter.com/SportYout79296

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZMYR8WTs8

+12

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

140Dawit Dave፤ Yewubdar Getnet እና 138 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.