“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን”

“አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን” ስንል የነዋሪዎቿን ህይወት እና አኗኗር ማሳመርንም የሚያካትት ነው።

ለዚህ አንዱ ማሳያ የሆነው ለካሳንችስ ልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የገነባነዉን ማዕከል ነዉ።

ዛሬ አገልግሎት የምናስጀምረው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ:-

• በ1200 መኖሪያ ቤቶች 6500 ነዎሪዎችን የያዘ መኖሪያ መንደር ነው።

• 1.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የአስፋልት መንገድ አለው።

• ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል አለው።

• በ2 ወር ጊዜ ዉስጥ የተገነቡ ከቅድም አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነምገባ ማዕከሉ ይዟል።

• በ3 ሺፍት ለ270 እናቶች የስራ እድል የፈጠረ የእንጀራ መጋገርያ ፋብሪካ አለው።

• 500 አረጋዉያን እና አቅመ ደካሞችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል የምገባ ማዕከል አለው።

• በቀን 60 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ እና የዕህል ወፍጮዎችን ይዟል።

• ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት መጫወቻ እና የህጻናት ማቆያ አለው።

• ⁠ሁለት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንዲሁም አረንጓዴ ቦታዎችና መናፈሻዎች ተገንብተዋል።

• በቋሚ እና በጊዜያዊነት ለ1646 ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

+16

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

121Dawit Dave፤ Waaqkenee Dhuguma Saadeeta እና 119 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.