
ስነ-ተዋልዶ ጤና እና ዩ ሪፓርት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ
ስነ-ተዋልዶ ጤና እና ዩ ሪፓርት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ
ሕዳር 28 ቀን 2017 ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለአሰልጣኞች ለፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊዎች አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች የስነ ተዋልዶ ጤና እና ዩ ሪፓርት ላይ የሚያተኩር ስልጠና ሰጠ
ዩ ሪፓርት በዲጂታል መድረክ ወጣቶችን ለማሳተፍ እና ድምፃቸውን ለማጉላት እንደሚያስችል ገለጻ ያደረጉት ወይዘሮ ሕይወት በዩኒሴፍ የበለጸገው መተግበሪያ የፖሊሲ እና የፕሮግራም ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ትኩረት በማድረግ እንደሚሰራ ተናግረውል
የልጆች መብትን ለመደገፍ በሚወጡ ፓሊሲዎች ላይ የወጣቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ በሚያግዘው መተግበሪያ በመሳተፍ ዲጂታል ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል
በሥነ ተዋልዶ ላይ የሚያተኩረውን ስልጠና የሰጡት የጤና ቢሮ ባለሙያ
ወጣቶች ከእድሜያቸው ጋር ተያይዞ ለተለያዩ ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ችግሮች ተጋላጭ እንዳይሆኑ በትኩረት መሰራት ይገባል ብለዋል
አፍላ ወጣቶች ካላስፈላጊ እርግዝና ፣ከኤች አይ ቪ ኤድስና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ፣ እንዲሁም ከተለያዩ አደንዛዥ ዕፅና አልኮል መጠጥ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሰልጣኟ ጥሪ አቅርበዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
42Gossaye Alemayehu፤ Yewubdar Getnet እና 40 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.