የሕይወት ክህሎት የአሰልጣኝነት ስልጠና መሰጠት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የሕይወት ክህሎት የአሰልጣኝነት ስልጠና መሰጠት ጀመረ

የሕይወት ክህሎት የአሰልጣኝነት ስልጠና መሰጠት ጀመረ

ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የህይወት ክህሎት የአሰልጣኝነት ስልጠና መሰጠት ጀመረ

በስልጠናው በታዳጊ ወጣቶች ልማት መርሃ ግብር የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች መሳተፋቸውን የገለጹት በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የጤና ቡድን መሪ ጤና መኮንን ሃያት ኪያር ስልጠናውን የወሰዱ አሰልጣኞች በስራቸው የሚገኙ ታዳጊ ስፓርተኞችን የማብቃት ስራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል

አሰልጣኞቹ ለሕይወት ክህሎት ስልጠና የተዘጋጀውን ማንዋል የማዳበር ኃላፊነት አለባቸው ያሉት ወይዘሮ ሐያት ታዳጊዎች በአመለካከት ብቁ ለማድረግ በሕይወት የሚያጋጥማቸውን ፈተና ማለፍ የሚያስችል ክህሎት ከስፓርቱ ጎን ለጎን እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል

የህይወት ክህሎት ስልጠና የዕለት ከዕለት ኑሮ ውስጥ የሚያጋጥሙንን ኃላፊነቶችን እና ፈተናዎችን በብቃት ለመወጣት የሚያስችሉ ስልቶች የሚገምበት ነው ያሉት ወይዘሮ ሃያት የአሰልጣኝነት ስልጠና ያጠናቀቁ አሰልጣኞች ያገኙትን እውቀትና ክህሎታቸውን በመጠቀም ታዳጊዎችን በማገዝና ለማብቃት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል

ስልጠናውን የሰጡት የሳይኮሎጂ ባለሙያ አቶ አበበ ተረፈ የክህሎት አይነቶች፣የባህሪ ለውጥ፣ መላካምነት ፣ችግር አፈታት፣የተግባቦት ችሎታ ማዳበር፣ውሳኔ ሰጪነት የስልጠና አስጣጥ ዘዴ፣ አሰልጣኞቹ ከሌሎች ጋር አብሮ የመኖር ግንኙነት ክህሎት፣ ከሁኔታዎች ከሁኔታዎች ጋር የመላመድ ክህሎት ፣ ለራስ ህይወት ኃላፊነት መውሰድ ክህሎት፣ ራስን የመግዛት ክህሎት (Self control skill) ስሜትን የመቋቋም ክህሎት፣ (Coping with Emotions skill) ርዕሶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በልዩ ስልጠና መርሃ ግብር በስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከላት ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመቀናጀት የመጀመሪያ ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠና ስኬታማ መሆኑን የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል

የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_

+6

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

64Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 62 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.