የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 16ኛ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    1

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስፖርት ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ

ታህሳስ 03 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

ስፖርት የስብእና መገንቢያ ከመሆኑ አኳያ ትውልድ የሚገነባባቸው ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለማስፋፋት አበረታች እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ በ16ኛው የቂርቆስ የስፖርት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸው ላይ ተናግረዋል ።

ዋና ስራ አስፈጻሚ አያይዘውም የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት በማንገብ በዘርፉ የሚሰሩ ሁለንተናዊ የስፖርት ልማት ስራዎች የሚፈለግበት ውጤት ለማምጣት እና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ አስተዳደሩ በትኩረት ይሰራል ብለዋል ።

አቶ ጠብቀው አመሸ የክፍለ ከተማው ክለቦቻችን በአፍሪካ ጭምር ዝናቸው የናኘ እንደሆነ በመጥቀስ በስፖርት ዘርፉ ስራ ዕድል የመፍጠር እና የወጣቶችን ተጠቃምነት የማረጋገጥ ተግባር መሰራቱን ተናግረዋል ።

የ2016 የቂርቆስ የስፖርት ምክር ቤት ማጠቃለያ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዚሁ ሪፖርት 400 ለሚሆኑ ወጣቶች እና ሴቶች ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን ፣ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች የንቅናቄና ተሳትፎ ስራ መከናወኑ ፣ የክለቦች የሻምፕዮንነት ውድድር እና በዚሁ የተገኘ ውጤት ፣ የተገነቡ እና እድሳት የተደረገላቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ወዘተ በይዘትነት የተካተተበት ለስፖርት ምክር ቤቱ አባላት ቀርቧል ።

ከዚህ በተጨማሪም ከ2012 እስከ 2015 በጀት አመት ኦዲት ሪፖርት ግኝት ምን እንደሚመስል ለጉባኤተኛው ቀርቧል።

የስፖርት ምክር ቤት አባላት በበኩላቸውም ከዘርፉ ጋር ተያይዞ በወንዶች እጅ ኳስ እና በሴቶች እግር ኳስ ክለቦች ላይ ያሉ ተስፋዎች እና ተግዳሮቶችን የተለያዩ ሃሳብ ጥያቄዎችን አንፀባርቀዋል ።

ለተነሱ ሃሳብ ጥያቄዎችም መድረኩን በመሩት በክፍለ ከተማው ስፖርት ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ እና የወጣቶች እና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በአቶ ጠብቀው አመሸ ፣ በክፍለ ከተማው ኦዲት ባለሙያው በአቶ ፊጣ እና በስፖርት ምክር ቤቱ ፀሃፊ በአቶ ጌታመሳይ በኩል ምላሽ ከተሰጠ በኋላ የቀረበውን የ2017 የስፖርት ምክር ቤቱ እቅድ በአባላቱ እንዲፀድቅ ተደርጓል ።

በመጨረሻም በ2016 በጀት ዓመት ውጤታማ ለነበሩ ተቋማት እና ግለሰቦች ዕውቅናና ሽልማት በመስጠት ጠቅላላ ጉባኤው ተቋጭቷል ።

ቂርቆስ ኮሙኒኬሽን

+3

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

57Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 55 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.