
15ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የስፓርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ
15ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የስፓርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ
ታህሳስ 5 ቀን 2017 ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ 15ኛው ስፖርት ምክር ቤት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአድዋ ድል መታሰቢያ የምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ስፖርት ምክር ቤት ሰብሳቢ ወ/ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት የከተማችንን የስፖርት እድገት ለማረጋገጥ እና በአካል እና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለመገንባት የተሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጽዋል።
በከተማችን የተገነቡት 1,314 የህፃናት እና ወጣቶች የመጫዎቻ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ለዘርፉ የሰጠነውን ትኩሩት የሚያሳይ የስፓርት ቤተሰቡን ፍላጎት ያማከለ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የስፖርት ምክር ቤቱ ም/ሰብሳቢ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው የስፓርት ምክር ቤት ትልቁ ኃላፊነት ለስፓርት ዕድገትና መስፋፋት ሃሳቦችን ማፍለቅ እና ስፓርቱን ከመንግስት ደጎማ ማላቀቅ መሆኑን ተናግረው ለከተማ አስተዳደሩ ሁለንተናዊ ስፓርት ዕድገት በጋራ እንስራ ብለዋል።
ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ከተማ አስተዳደሩ በተለይ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለስፖርቱ ሁለንተናዊ እድገት በሰጡት ልዩ ትኩረት እንደ ከተማ በስፖርቱ ዘርፍ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለ አቶ በላይ ተናግረዋል።
የስፓርት ልማት እቅዱን ለማሳካትና የወጣቱን፣ የስፓርት ቤተሰቡን ተሳትፎ እና ተጠቃሚናት ለማድረጋገጥ የጀመራቸውን ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ በላይ በመልዕክታቸው ገልፀዋል።
የምክር ቤቱን የ2016 ሪፖርት እና የ2017 እቅድ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና የምክር ቤቱ ጽሐፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በስፖርት ዘርፍ የሕዝቡን ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል
15ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የስፖርት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባኤ ጉባኤው የ2015ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ፣ የ2016ዓ በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርት፣ የ2017 በጀት አመት ዕቅድ እና የ2015ዓ.ም ኦዲት ሪፓርትን ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አፅድቆል ።
ጉባኤው በ2016 ዓ.ም ውጤት ያስመዘገቡ ክለቦችን፣ ተቋማትን እና የስፖርት ማህበራትን የእውቅና ሰጥቷል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር :- https://twitter.com/SportYout79296
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZMYR8WTs8/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addisabebayouthandsport/#
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.