የ14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የ14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ

የ14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ

የካ ክፍለ ከተማ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል

ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ሕጻናት እና ማህብራዊ ጉዳይ ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተናግጅነት ሲካሄድ የቆየው

14ኛው የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው ስፖርታዊ ውድድርና ፌስቲቫል በየካ ክፍለ ከተማ አጠቃላይ አሸናፊ ተጠናቀቀ

የአካል ጉዳተኞች የስፖርት ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ከህዳር 24 እስከ ታህሳስ 7 / 2017 ዓ.ም ድረስ በሰባት የጉዳት አይነት ከ8ሺ በላይ የስፓርት ልዑካን ሲካሄድ ሰንብቶ ዛሬ በቤለር ሜዳ በድምቀት ተጠናቋል

የአካል ጉዳተኞችን ማህበራዊ ኢከኖሚያዊ፣ስነ ልቦናዊ እና ፓለቲካዊ ጥቅማቸውን ለማረጋገጥ ቢሮዋቸው በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የገለጹት የአዲስ አበባ ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወይንሸት ዘሪሁን የአካል ጉዳተኞችን መብት ማስጠበቅ ስብአዊ የልማት አጀንዳ መሆኑን አስገንዝበዋል

ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ስፓርትን በመምራትና የሚሰሩ ሜዳዎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ በማድረግ ላከናወነው ተግባር እውቅና የሰጡት ወይዘሮ ወይንሸት የአካል ጉዳተኞችን ማህበር ለማጠናከር መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል

አካል ጉዳተኞች በአገራችን ሁለንተናዊ እድገት ላይ ሚናቸው የጎላ መሆኑን የገለጹት የስፖርት ማህበራት ማደራጃና ውድድር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ታደለ እርስ በእርስ ከተደረው ስፓርታዊ ፉክክር ባለፈ አካል ጉዳተኞች መስተጋብራቸውን ያጠናከሩበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል

በፖራሊምፒክ ስፖርቶች 25 ወርቅ 16 ብር እና 11 ነሐስ በማስመዝገብ የካ ክፍለ ከተማ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን፣ 22 ወርቅ 15 ብር እና 10 ነሀስ በመስብሰብ ልደታ ክፍለ ከተማ 2ኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ቦሌ ክፍለ ከተማ 15 ወር 19 ብር እና 10 ነሐስ በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት መስማት በተሳናቸው ውድድር 11 ወርቅ 10 ብርና 6 ነሐስ በማምጣ ቦሌ ክፍለ ከተማ አንደኝነት ሲያጠናቅቅ ፣ 4 ወርቅ 2 ብር እና 1 ነሀስ በማስመዝገብ 2ኛ በመሆን ኮልፌ፣ 3 ወርቅ 3 ብር እና 5 ነሀስ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ አራዳ ክፍለ ከተማ 3ኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡

በክብደት ማንሳት በወንዶች በአራት ወርቅ እና በአንድ ብር የካ ክፍለ ከተማ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን በሴቶች 2 ወርቅ እና 1 ብር የሰበሰበው ልደታ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል

በእግር ጉዳት የንግድ ጉተታ በወንዶች ጉለሌ በሴቶች ኮልፌ የዋንጫ ባለቤት ሲሆኑ፣ዶሚኖስ በወንዶች ንፋስ ስልክ በሴቶች ቦሌ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል

በካርታ ወንዶች ልደት ሲያሸንፍ አራዳ የሴቶችን ዋንጫ ወስዷል፤ በዳርት ስፓርት ውድድር በወንዶች የካ በሴቶች አዲስ ከተማ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል

በጠረጴዛ ቴኒስ በእግር ጉዳት የወንዶች ውድድር ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በበላይነት ሲያጠናቅቅ መስማት የተሳናቸው ወንዶች አራዳ መስማት የተሳናቸው ሴቶች የካ ክፍለ ከተማ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል

በአትሌቲክ ስጋደዌ ተጠቂ በሁለቱም ጾታ ኮለፌ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን ፣ በአትሌቲክስ አዕምሮ ዕድገት ውስንነት በወንዶች ቦሌ በሴቶች ንፋስ ስልክ የዋንጫ ተሸላሚ ሲበረከትላቸው በአትሌቲክስ ድክዬ በአትሌቲክስ እጅ ጉዳት ወንዶችና በሴቶች የካ ሻምፒዮና መሆን ችሏል

በሽብርቅ የዋንጫ ሽልማት በዳኞች በተሰጠ ነጥብ ለሚ ኩራ እና ኮልፌ 3ኛ በእኩል ነጥብ 3ኛ ሲወጡ አቃቂ ቃሊቲ እና ልደታ 2ኛ እና 1ኛ በመሆን አጠናቀዋል

በውድድር ስፖርት ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የስፖርታዊ ጨዋነት ዋንጫን ሽልማት አቃቂ ክፍለ ከተማ ሲያገኝ ፣ የመጪው አመት የ14ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞች እና መስማት የተሳናቸው ስፖርት ፌስቲቫልና ውድድር ሻምፒዮና የካ ክፍለ ከተማ የቀጣይ አዘጋጅ መሆኑ ታውቋል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+28

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

70አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 69 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.