የሕይወት ክህሎት የአስልጣኝነት ስልጠና ያጠናቀቁ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የሕይወት ክህሎት የአስልጣኝነት ስልጠና ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ተመረቁ

የሕይወት ክህሎት የአስልጣኝነት ስልጠና ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ተመረቁ

ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሕይወት ክህሎት የአሰልጣኝነት ስልጠና ሲያሰለጥናቸው የሰነበተውን ሰልጣኞች አስመረቀ

በተግባር እና በንድፈ ሐሳብ ሲሰጥ የቆየውን የአሰልጣኝነት ስልጠና ያጠናቀቁ አሰልጣኞች በስራቸው የሚስለጥኑ ታዳጊዎችን የማሰልጠን ኃላፊነት እንዳለባቸው የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ ገልጸዋል

አቶ ጎሳዬ አያይዘውም ስልጠናው አሰልጣኞች ከመደበኛው ስራቸው በተጨማሪ ታዳጊ ስፓርተኞች በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ብቁ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚያደርጉትን ጥርት እንደሚደግፍ ተናግረዋል

በአሰልጣኝነት ስልጠናው የታዳጊ ወጣቶች ልማት መርሃ ግብር የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች መሳተፋቸውን የገለጹት በወጣቶችና ጤና መኮንን ሃያት ኪያር ስልጠናውን የወሰዱ አሰልጣኞች በስራቸው የሚገኙ ታዳጊ ስፓርተኞችን የማብቃት እና ለሕይወት ክህሎት ስልጠና ተብሎ የተዘጋጀውን ማንዋል እንደሚያዳብሩ ገልጸዋል

ስልጠናውን የሰጡት የሳይኮሎጂ ባለሙያ አቶ አበበ ተረፈ የክህሎት አይነቶች፣የባህሪ ለውጥ፣ መላካምነት ፣ችግር አፈታት፣የተግባቦት ችሎታ ማዳበር፣ውሳኔ ሰጪነት የስልጠና አስጣጥ ዘዴ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል

የህይወት ክህሎት ስልጠና የዕለት ከዕለት ኑሮ ውስጥ የሚያጋጥሙንን ኃላፊነቶችን እና ፈተናዎችን በብቃት ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት አሰልጣኙ አብሮ የመኖር ግንኙነት ክህሎት፣ ከሁኔታዎች ከሁኔታዎች ጋር የመላመድ ክህሎት ለራስ ህይወት ኃላፊነት መውሰድ ክህሎት፣ ራስን የመግዛት ክህሎት ስሜትን የመቋቋም ክህሎት፣ ርዕሶች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_

+20

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

72Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 70 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.