በአስተሳሰቡ የተቀየረ ወጣት የበለጸገች አገርን...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

በአስተሳሰቡ የተቀየረ ወጣት የበለጸገች አገርን በመገንባት ሂደት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

በአስተሳሰቡ የተቀየረ ወጣት የበለጸገች አገርን በመገንባት ሂደት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዓለም አቀፉ ወጣቶች ሕብረት በምጽሐረ ቃል /IYF/ እና ከልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የማይንድ ሴት ስልጠና ሰጠ

መቀመጫውን ኮርያ ካደረገው IYF ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በተሰጠው የአዕምሮ ውቅር ስልጠና ላይ ከ1500 በላይ የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን በአስተሳሰቡ የተቀየረ ወጣት የበለጸገች አገርን በመገንባት ሂደት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ተመልክቷል

የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወልደሃና ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር የኢትዮጵያን ባህል ጠንቅቀው በሚያው የኮርያ አሰልጣኞች እየተሰጠ የሚገኘው የአስተሳብ ቀረጻ ስልጠና በሁሉም ክፍለ ከተማ እየተሰጠ እንደሚገኝ አስታውሰው ወጣቶች ለለውጥ ራሳቸው በማዘጋጀት ነገን የተሻለ ለማድርግ በትጋት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡

በአስተሳሰቡ የተገነባ ወጣት ራሱን አከባቢውን እና አገሩን መቀየር ይችላል ያሉት አቶ መክብብ ካልችልም መንፈሰ ወጥተን እንችላለን የሚል አስተሳበብ በመላበስ በከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የሦስት ወር የስራ እድል አማራጭ ተጠቃሚ በመሆን እራስንም አገርንም መለወጥ ይገባል ብለዋል፡፡

ወጣቱን ብቁ እና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የማይንድ ሴት ስልጠናዎች በስፋት እየተሰጡ መቆየታቸውን ያስታወሱት የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክብረዓለም ደምሴ ከኮርያ ድረስ መጥተው የልደታ ክፍለ ከተማ ወጣቶችን ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞችና በወጣቶች ላይ በትኩረት እየሰራ ለሚገኘው ቢሮ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ኢትዮጵያውን ከኮርያ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት እንዳላቸው ያወሱት አቶ ክብረ ዓለም ወጣቶች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ልምድ ተግባራዊ በማድረግ በሚፈጠሩ ስራ እድሎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የማይንድ ሴት ስልጠናውን የሰጡት የዓለም አቀፉ ወጣቶች ህብረት ዳይሬክተር ዶክተር ናም አልማዝ ከመቀረጹ በፊት ዋጋው ዝቅ ያለ ቢሆንም ከተቀረጸ ቡኃላ ዋጋው እንደሚጨምር አውስተው ለውጥ ለማምጣት የወጣቱን አስተሳሰብ መቀየር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን ከተጠቀመች እና ያላትን በርካታ የሰው ኃይል በመጠቀም ከኮርያ የስራ ባህል ትምህርት ከተወሰደ በዓለም ቀዳሚ መሆን ትችላለቸ ያሉት ዶክተር ናም ኮርያ አመለካከት ላይ በመስራቷ ማዕድን በሌለበት አገር ኤክስፖርት እንደምተደርግ አስገንዝበዋል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+10

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

55Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 53 ሌሎች

 

 

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.