
የስፓርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
የስፓርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ
ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ የስፓርት ዘርፍ ባለሙያዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚያተኩር ስልጠና ሰጠ
የከተማችን ስፓርት በሁለም የስፓርት መስክ ውጤታማ ለማድረግ በሚሰራው ስራ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፋ በአዲስ አበባ ስፓርት ምክር ቤት ይፋ የተደረገው የከተማው ብራንድ መለያ ለስፓርቱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል
ከወረዳ እስከ ማዕከል ያለውን የሰው ኃይል ችግር ለመቅረፍ ከፐብሊክ ሰርቪስ ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት አቶ ዳዊት ለአዲስ አበባ ሁሉንተናዊ ስፖርት ዕድገት በየደረጃው ያለው ባለሙያ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል
የስፓርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ በከኩላቸው ብቃት ያላቸው ተተኪ ስፓርተኞችን ለማፍራት የስፓርት ባለሙያዎች ማብቃት ወሳኝ መሆኑ ገልጸው በሁሉንተናዊ ስፖርት ዕድገት ዙሪያ የሚሰጡ ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል
ለባለሙያዎቹ የተዘጋጀውን ስልጠና ዶክተር መስፍን ገዛኽኝ እና ኢንትራክተር ሙሉነህ ግርማ የሰጡ ሲሆን ያላቸውን የዳበረ ልምድ እና እውቀት በመጠቀም ለስፓርት እድገት በሚበጁ ቴክኒካል እና የእውቀት ክፍተቶች ላይ ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
73Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 71 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.