ሕገ ወጥ ስደት በወጣቶች ላይ ማህበራዊ እና ስነ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ሕገ ወጥ ስደት በወጣቶች ላይ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ

ሕገ ወጥ ስደት በወጣቶች ላይ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ

ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና በስደት ዙሪያ የወጡ አዋጆችና መመሪያዎች ላይ የሚያተኩር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ

በልደታ ክፍለ ከተማ አዳራሽ በተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ከቂርቆስ፣ከአራዳ፣ንፋስ ስልክ ከአዲስ ከተማ እና ከኮልፌ ክፍለ ከተማ የተውጣጡ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ህግ ወጥ የሰዎች ዝውውር ኦኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጫና ከማሳደሩም ባሻገር ዜጎች ለአካላዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት እየዳረገ እንደሚገኝ ተመልክቷል

ሕገ ወጥ ስደት የአገሪቱን ወጣት እና የተማረ የሰው ኃይል እያሳጣት መሆኑን የገለጹት የወጣቶች ግንዛቤና ንቅናቄ ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጤናዬ ታምሩ ወጣቶች ሀገር ተረካቢና ባለአደራ እንደመሆናቸው መጠን የጉዳዩን አስከፊነት በመገንዘብ ከህገ ወጥ ስደት ራሳቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ወጣቶችን በአደገኛ ጉዞ ከኢትዮጵያ ለመሰደድ ከሚያበቋቸው ምክንያቶች ውስጥ በውጭ ዓለም ሥራ እና ገንዘብ በቀላሉ ይገኛል የሚሉ የተጋነኑ መረጃዎችን ጨምሮ ፣ ስራ አጥነት የአቻ ግፊት ድህነት መሆናቸውን አቶ ጤናዬ አስገንዝበዋል

ስልጠናው የሰጡት በፍትህ ቢሮ በሰው መነገድና ሰውን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል መከላከል ጽ/ቤት አቃቢ ሕግ አቶ ነብዩ በቀለ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ የማዘዋወር ወንጀል ስለመሆኑ ባሉት የሕግ ማዕቀፎች ላይ.ሰፊ ማብራርያ ሰጥተዋል

አደገኛ በሚባሉ የፍልሰት መስመሮች በርካታ ኢትዮጵያውያን የበረሃ እና የባህር ጉዞ እ በማድረግ ካሰቡበት ቦታ መድረስ እንዳልቻሉ ያወሱት አቶ ነብዩ ስደት ውስብስብ ወንጀል እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል

የስልጠናው ተሳታፊ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ወቅታዊ እና አስፈላጊ በመሆኑ በስፋት ሊሰጥ እንደሚገባ ገልጸው መንግስት ኤጀንሲዎች ላይ ቁጥጥር እንዲያደርግ እና በስራ እድል ፈጥራ የጀመራቸውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል

አቶ ጤናዬ ባደረጉት ማጠቃለያ ንግግር ወጣቶች የሰጡት አስተያየት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው ህገ ወጥ ስደትን በዘላቂነት ለመከላከል እና የስራ ባህልን ለማዳበር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

+10

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

40Dawit Dave፤ አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ Addis Ababa Youth and Sport Bureau . እና 38 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.