
ጥራት ያለው ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ለተቋም ግንባታ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ
ጥራት ያለው ፈጣን አገልግሎት አሰጣጥ ለተቋም ግንባታ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገለጸ
ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በስፓርት ዘርፍ ለሚሰሩ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ቡድን መሪዎች በአገልግሎት አሰጣጥ እና በዩ ሪፓርት ላይ የሚያተኩር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ
ባለፉት የለውጥ ዓመታት ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ያከናወናቸው ስራዎች ውጤታማ ተቋም መገንባት አስችሎናል ያሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፓርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፋ ስፓርቱ ሕዝባዊ መሰረት እንዲኖረው የግል ባለሃብቱን ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል
በወረዳና በክፍለ ከተማ ያሉ ባለሙያዎች ባከናወኑት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተመዘገቡ ለውጦችን ያወሱት አቶ ዳዊት በቀጣይ የሚከናወኑ የባህል ስፖርት፣ የተማሪዎች ስፖርት፣የሴቶች ስፖርት በስኬት ለማከናወን የተጀመረው ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል
በከስተመር ሰርቪስ ላይ የሚያተኩረውን ስልጠና የሰጡት ዶክተር መስፍን ገዛኽኝ የተቋምን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመንና ለማሻሻል በሚያስችሉ ነጥቦች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገው አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ ፈጣን ምላሽ መስጠት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል
በተያያዘ ዜና በዩኒሴፍ በበለጸገው ዩ ሪፓርት በዲጂታል መድረክ ወጣቶችን ለማሳተፍ እና ድምፃቸውን ለማጉላት የፖሊሲ እና የፕሮግራም ቀረጻ ላይ ያለውን ፋይዳ አብራርተዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
98You፤ Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 95 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.