የጃንሜዳ መሮጫ ትራክ በፍጥነት እና በጥራት ለማ...

image description
- ውስጥ ስፖርት    0

የጃንሜዳ መሮጫ ትራክ በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ

የጃንሜዳ መሮጫ ትራክ በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ

ታህሳስ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በጃን ሜዳ እያሰሩት ያለው መሮጫ ትራክ በጥራት እና በፍጥነት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዘርፉ ስፖርት ወሳኝ የሆነው መሮጫ ትራክ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለመስራት እያደረገ ያለው ለሌሎች ፌዴሬሽኖች ምሳሌ እንደሚሆን የማዕከላትና ስፓርት ማዘውተሪያ ስፍራ አስተዳደር ልማት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ባዩ ገልጸዋል

የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚ በዘረጋው ቅንጅታዊ አሰራር ጃንሜዳን ለአትሌቶች ስልጠና እና ለውድድር ምቹ በማድረግ የሰራው ስራ መጠናከር አለበት ያሉት አቶ ብርሃኑ አትሌቶችን ውጤታማ ለማድረግ ልምምድ የሚሰሩበት ቦታ እና ውድድር የሚያደርጉበት ቦታ ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል

የአትሌቲክሱ ትልቅ ፈተና የሆነውን በቂ የማዘውተርያ ስፍራ ችግር ለመቅረፍ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ አቻው ጋር እያሰራ ያለው ትራክ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝ አትሌት መልካሙ ተገኝ ገልጸዋል

ውጤታማ ውድድሮች ለማድረግ እና ተተኪ ስፓርተኞችን በጥራትና በብዛት ለማፍራት አዲሱ ስራ አስፈጻሚ በትኩሩት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ፕሬዘዳንቱ ከአትሌቲክሱ ጋር ታሪካዊ ትስስር ባለው ጃንሜዳ የሚሰራው ትራክ 2 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍን ገልጸዋል

ምርጫ ትራኩ 3.5 ሚሊዮን ብር ወጪ እየተሰራ እንደሚገኝ ያወሱት አትሌት መልካሙ ፌዴሬሽኑ የሚሰራቸውን ስራዎች የግል ባለሃብቱና በስፓርት ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶች እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል

እየተሰራ ባለው ትራክ ልምምድ ሲያደርጉ ያገኘናቸው አትሌቶች ፌዴሬሽኑ መሮጫ ትራክ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱ ልምምድ እና ለውድድር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው በዚህ ስራ የተባበሩ አካላትን አመስግነዋል

የጃንሜዳ ሀገር አቋራጭ ውድድ ከታህሳስ19-20 2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚካሄድ ተመልክቷል

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር :- https://twitter.com/SportYout79296

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZMYR8WTs8/

👍👍👍 ኢሜል addissport2013@gmail.com

+12

ሁሉም የስሜት መግለጫዎች

89Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 87 ሌሎች


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.