
ቢሮው ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የእውቅና ሽልማት አበረከተ
ቢሮው ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የእውቅና ሽልማት አበረከተ
ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ እውቅና ሰጠ
በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በቢሮ እና በፌዴሬሽኑ የተዘጋጀ የክብር ካባ እና የአንገት ሃብል ሽልማት ተበርክቶላታል
በጉባኤው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ባለፉት አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑ በብቃት በመምራት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ላበረከተችው አስተዋጽዖ የተበረከተ ሽልማት መሆኑን ገልጸዋል
በኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የሚመራው ፌዴሬሽኑ በአዲስ አበባ ስፖርት ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳበረከቱ ያወሱት አቶ በላይ ለአገር የከፋሉትን ዋጋ ጀግኖችን ማክበር በሁሉም መስክ ሊለመድ ይገባል ብለዋል
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለዓለም አትሌቲክስ እና ለአትሌቲክስ ስፖርት ላበረከተችው አስተዋፅኦ እውቅና መሆኑን ገንጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር :- https://twitter.com/SportYout79296
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZMYR8WTs8/
ኢሜል addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
212Dawit Dave፤ Gossaye Alemayehu እና 210 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.