
ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ በተለያዩ አጀዳዎች ላይ ውይይት አካሄደ።
ቢሮው የአገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ በተለያዩ አጀዳዎች ላይ ውይይት አካሄደ።
ታህሳስ 14 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች እና ከቢሮው ዳይሬክቶሬቶች ጋር ውይይት አካሄደ።
ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን የከተማውን ወጣቶች እና የስፖርት ቤተሰቦች ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከከተማ እስከ ብሎክ የአገልግሎት አሰጣታችንን ማዘመን ይገባል ብለዋል።
የመልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃ በደረጃ መፈታት እንዳለባቸው የተናገሩት አቶ በላይ በተለይ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ላይ ሁሉም አመራር ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በውይይቱ የተሳተፋ የፅ/ቤት ሀላፊዎች እና ዳይሬክተሮችም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እንዲሁም ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን ለመታገል እቅድ አውጥተው እየሰሩ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን በቀጣይ አጠናክረው አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
የቢሮው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አቶ በላይ ያስቀመጠ ሲሆን የወጣቶች የውይይት መድረክ ከብሎክ እስከ ከተማ እንደሚካሄድ እና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት ፍሬዎች የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል እንደሚዘጋጅ ታሳቢ በማድረግ ሁሉም አካል ፕሮግራሞችን ለማሳካት እርብርብ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
ሁሉም የስሜት መግለጫዎች
109Gossaye Alemayehu፤ Waaqkenee Dhuguma Saadeeta እና 107 ሌሎች
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.