
ከጃፖን ሀገር በመጡ የስፖርት በጎ ፍቃደኛ አሰልጣኞች በመዲናዋ ለሁለት አመታት የሚቆይ ለታዳጊ ወጣቶች የቴኒስ ስፖርት ስልጠና ሊሰጡ ነው።
ከጃፖን ሀገር በመጡ የስፖርት በጎ ፍቃደኛ አሰልጣኞች በመዲናዋ ለሁለት አመታት የሚቆይ ለታዳጊ ወጣቶች የቴኒስ ስፖርት ስልጠና ሊሰጡ ነው።
ታህሳስ 15 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የጃፖን መንግስት የልማት ተርአዶ ድርጅት (ጃይካ) የታዳጊ ወጣቶች የስልጠና መርሀ ግብርን ለመደገፍ በተደረገ ስምምነት የበጎ ፈቃደኛ የስፖርት አሰልጣኞች በአዲስ አበባ ከተማ ለሁለት አመት የሚቆይ የቴኒስ ስፖርት የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ሊሰጥ ነው።
የበጎ ፍቃደኛ አሰልጣኞችን በቢሮቸው የተቀበሉት አቶ ዳዊት ትርፉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ ለታዳጊ ወጣቶች የቴኒስ ስልጠና በበጎ ፍቃደኝነት ለመስጠት ከጃፖን ሀገር ወደ አዲስ አበባ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
አሰልጣኞች በሚኖራቸው ቆይታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ የገለፁት አቶ ዳዊት ስልጠናው በቴኒስ ስፖርት ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ለማፍራት እንደሚረዳ ገልፀዋል።
አሰልጣኞችም በአዲስ አበባ ከተማ በሚኖራቸው ሁለት አመት ቆይታ እውቀታቸውን ልምዳቸውን እና ተሞክሯቸውን በመጠቀም የቲኒስ ስፖርትን በከተማው ለማስፋፋት እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
አሰልጣኞች መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ቴኒስ ማዕከል በማድረግ በከተማዋ ለሚገኙ ታዳጊዎች የቴኒስ ስፖርት ስልጠና እንደሚሰጡ ተመላክቷል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.