
በወጣቶች የተመሰረቱ ኪነ ጥበብ ቡድኖች ለአገር ገጽታ ግንባታ እና መልካም እሴቶችን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና አላቸው/አቶ በላይ ደጀን
በወጣቶች የተመሰረቱ ኪነ ጥበብ ቡድኖች ለአገር ገጽታ ግንባታ እና መልካም እሴቶችን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና አላቸው/አቶ በላይ ደጀን
ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ
ብልፅግናና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ በአስረ አንዱም ክፍለ ከተማ በሚገኙ የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት እየተካሄደ የሚገኘው ፌስቲቫል ለሃገርን ገጽታ ግንባታና መልካም እሴቶች ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተገለጸ
በበጋው ለሚያካሂደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ፌስቲቫል እና ውድድር በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ወጣት ስብዕና ማዕከላት የሚሰሩ ወጣቶች እየተሳተፋ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገልጸዋል
ኪነ ጥበብ ለሃገርን ገጽታ ግንባታና መልካም እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ የጎላ ሚና እንዳላቸው አቶ በላይ አውስተዋል
አቶ በላይ አያይዘውም በከተማ ደረጃ በሚካሄደው የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል እና ውድድር በዘመናዊ ዳንስ እና ባህላዊ ውዝዋዜ አማተር የኪነ ጥበብ ቡድኖች እንደሚሳተፈ ገልጸዋል
በ114 የወጣት ስብዕና ግንባታ ማዕከላት ለኪነ ጥበብ ፍቅርና ዝንባሌ ያላቸውን አማተር ከያንያን እየተሳተፉ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ በላይ በኪነ ጥበብ የሚሳተፉ ወጣቶች ለሀገር የሰላም እና መልካም እሴቶችን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.