አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ ግልጸኝነት...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ ግልጸኝነት የሰፈነት አሰራር መዘርጋት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማ ለማድረግ ግልጸኝነት የሰፈነት አሰራር መዘርጋት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ/ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከተለያዩ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በዜጎች ስምምነት ሰነድ ላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት አገልግሎት አሰጣጡን ውጤታማና ተደራሽ ለማድረግ ግልጸኝነት የሰፈነበት አሰራር ወሳኝ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የዜጎችን ፍላጎት ለማርካት ቢሮ በወጣት እና በስፖርት ዘርፍ አዋጅ የተሰጠውን ተግባር ለመፈጸም የዜጎች ስምምነት ሰነድ ማዘጋጀት ወሳኝ መሆኑን የገለጹት

የአገልግሎት አሰጣጥ ክትልል ድጋፍና ምዘና ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልሀሚድ ድሌቦ አዳዲስ መመሪያዎች በማካተት የተዘጋጀው የዜጎች ስምምነት ሰነድ የተገልጋዩን ሕብረተሰብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ውጤታማ ለማድርግ እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡

ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት በሪፎርሙ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የገለጹት አቶ አብዱላሚድ ሁሉም አስፋጻሚ አካላት ወታቶችን ጉዳይ በእቅዳቸው ማካተታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡

የደንበኛውን ፍላጎት በማርካት መልካም አስተዳደርን ከመገንባት አኳያ የዜጎች የስምምነት ሰነድ አስፈላጊነት መሆኑን የገለጹት የፐብሊክ ሰርቪስ የስልጠና ባለሙያ አቶ ወንደሰን ሞገስ ስምምነቱን ከሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች ጋር በማቀናጀት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች በስታንዳርድ መሰረት በማድረግ የዜጎች ቻርተር ከአዘገጃጀት ጀምሮ እስከ አፈጻጸም ድረስ ያለው ሂደት መከታተል ያስፈልጋል ያሉት አቶ ወንደሰን የቅሬታ አቀራረብ እና አፈታት ስርዓት መዘርጋት ኪራይ ሰብሳቢነትን መታገል አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍 you tube

https://www.youtube.com/channel/UC0CARW3IdFaPlZ980VITn5Q

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.