
ለቴኳንዶ ስፓርት ቤተሰቦች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ለቴኳንዶ ስፓርት ቤተሰቦች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በስፓርት አዋጅ ፣ስፓርት ሳይኮሎጂ፣ኤክሰርሳይስ ፊዚዮሎጂ፣በቴኳንዶ መርህ እና በጸረ አበረታች ቅመሞች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ
በአራት ኪሎ ስፓርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በተሰጠው ስልጠና ላይ የስራ አስፈጻሚ አባላት፣ዳኞች፣አሰልጣኞች እና ስፓርተኞች መሳተፋቸውን የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የውብዳር ጌትነት ነግረውናል
ጽ/ቤት ኃላፊው አያይዘውም የስልጠናው ዓላማ የቴኳንዶ ስፓርትን ለማሳደግ እና በዘርፉ የሚሰሩ የስፓርት ባለሙያዎችን ማብቃት መሆኑን ገልጸዋል
በስፓርት ሳይኮሎጂ እና ኤክሰርሳይስ ፈዚዮሎጂ ያተኮረው ስልጠና በዶክተር ጥላሁን ፣ በስፓርት አዋጅ በዶክተር ወንደሰን ተፈራ በቴኴንዶ መርህ የዶ- ጽንሰ ሐሳብ ላይ ያተኮረው ስልጠና በማስተር ወጋየሁ ሰፊ ግንዛቤ መሰጠቱ ተገልጽዋል
በተያያዘ ዜና የአዲስ አበባ ውሹ ፌዴሬሽን እና ጁዶ አሶሴሽን በግንዛቤ ሜስጨበጫ ስልጠናው ላይ መሳተፋቸውን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል
ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው ስልጠና ላይ ከ120 በላይ የቴኳንዶ ስፓርት ቤተሰቦች መሳተፋቸው ተመልክቷል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.