
የወጣቶች አመለካከት የሚገነቡ እና በጎ አስተሳሰብን የሚያሰርጹ የማይንድ ሴት ስልጠናዎች ለከተማችን እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። /አቶ በላይ ደጀን/
የወጣቶች አመለካከት የሚገነቡ እና በጎ አስተሳሰብን የሚያሰርጹ የማይንድ ሴት ስልጠናዎች ለከተማችን እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። /አቶ በላይ ደጀን/
ታህሳስ 18 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
በሁሉም ክፍለ ከተሞች እየሰጠ የሚገኘው አስተሳሰብ ቀረጻ ስልጠና ወጣቶች በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያላቸውን አመለካከት እና አስተሳሰብ የመለወጥ ከፍተኛ አቅም እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ገለጹ
ከተማ አስተዳደሩ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ከ150ሺ በላይ ወጣቶች በቋሚ የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ያቀደውን ዕቅድ ለማስፈጸም የወጣቶችን ግንዛቤ ማሳደግ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ በላይ ወጣቱን በፖለቲካዊ ፣በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል
በማይንድ ሴት ስልጠናው በአሰረ አንዱም ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወጣቶችን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ በላይ ለስራ ፈላጊ ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የንቅናቄ እና የማይንድ ሴት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል
ቢሮው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችን በማይንድ ሴት ስልጠና ለማብቃት ከዓለም አቀፉ የወጣቶች ሕብረት ጋር የፈጸመው የሁለትዮሽ ስምምነት ውጤት ማሳየቱን አቶ በላይ ገልጸዋል
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.