ቢሮው ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋ...

image description
- ውስጥ ወጣቶች    0

ቢሮው ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ ለማስራት የሁለትዮሽ ስምምነት አካሄደ።

ቢሮው ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ ለማስራት የሁለትዮሽ ስምምነት አካሄደ።

ታህሳስ 21 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮሽ ስምምነት አካሄደ።

በሁለትዮሽ ስምምነቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፋት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ስምምነቱ በመዲናዋ በአደባባይ የሚከበሩ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት ታሪካዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ ለማድረግ እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በከተማው ውስጥ ያሉ የተደራጁ ወጣቶች እና በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ከሚቀሳቀሱ ወጣቶችን ጋር በማቀናጀት በከተማዋ ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደሚሰጥ የቢሮው ሀላፊው ገልፀዋል

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መዲና የዲፕሎማቶች መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን በርካታ አለም አቀፍ ጉባኤዎች የሚስተናገዱባት፣ በርካታ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት የሚከበሩባት ከተማ መሆኗን ያወሱት አቶ በላይ እነዚህን ሁነቶች በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ወጣቶችን ከሀይማኖት ተቋማት ጋር አቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

መጋቢ ታምራት አበጋዝ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ዋና ፀሀፊ በበኩላቸው ለከተማዋ ሰላም፣ ልማት እና ሁለንተናዊ እድገት ከከተማው ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት አመርቂ ወጤት ለማምጣት እንደሚረዳ ተናግረዋል።

የሁሉም ሀይማኖቶች አስተምሮ የሚያስረዳው ፈጣሪውን የሚፊራ፣ ስብዕናው የተገነባ ሀይማኖቱን እና ሀገሩን የሚጠብቅ ማህበረሰብ መፍጠር መሆኑን የገለፁት መጋቢ ታምራት በተለይ የወጣቶችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ከቢሮው ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ቢሮው ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የሁለትዮሽ የስምምነት ሰነድ አቶ ጤናየ ታምሩ የወጣቶች ግንዛቤና ንቅናቄ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ያቀረቡ ሲሆን በሀይማኖታዊ በዓላት አከባበር፣ በበጎ ፈቃድ ስራዎች፣ በመጤ በመጤ ባህሎችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዲሁም በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ዙሪያ በዋናነት ለመስራት መታቀዱን በዝርዝር አቅርበዋል።

በመጨረሻም አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ እና መጋቢ ታምራት አበጋዝ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ በጋራ ለመስራት በተዘጋጀው የሁለትዮሽ ስምምነት ሰነድ ላይ የፊርማ ስነ ስርዓት አካሂደዋል።

ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ 👇👇👇እናመሰግናለን

👍👍👍 ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219

👍👍👍 ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014

👍👍👍ትዊተር

https://twitter.com/compose/tweet

👍👍👍ቲክቶክ

https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/

👍👍👍ኢንስታግራም

https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/

👍👍👍 ኢሜል

addissport2013@gmail.com

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.