
የኢትዮጵያ ጨዋታ 2ኛ ዙር በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄድ የወጣቶች እና የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ሚናቸው የጎላ ነው። አቶ በላይ ደጀን
የኢትዮጵያ ጨዋታ 2ኛ ዙር በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲካሄድ የወጣቶች እና የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ሚናቸው የጎላ ነው። አቶ በላይ ደጀን
ታህሳስ 22 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የኢትዮጵያ ጨዋታ 2ኛ ዙር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አበበ ቢቂላ ስታድየም ከታህሳስ 18 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት ሲጠኒቀቅ ወደ ሶስተኛው ዙር ያለፉ 16 ክለቦች ታውቀዋል።
ውድድሩ በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የመዲናዋ ወጣቶች እና የስፖርት ክለብ ደጋፊዎች አስተዋኦቸው ከፍተኛ እንደነበር አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ገልፀዋል ወጣቶችን እና የስፖርት ቤተሰቦችን አመስግነዋል።
ውድድሩ በተካሄደበት በአበበ ቢቂላ ስታድየም በአራቱም ቀናት በአጠቃላይ ከ50ሺህ በላይ የክለብ ደጋፊዎች ወደ ስታድየም እንደገቡ የገለፁት አቶ በላይ ደጋፊዎች አንድነትን፣ አብሮነትን እና ወድማማችነት የሚገልፁ እንዲሁም ክለባቸውን የሚያበረታቱ መልዕክቶች ያስተላለፉበት ውድድር እንደነበር ገልፀዋል።
በቀጣይ ቢሮው በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ለከተማው ወጣቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች እና የክለብ ደጋፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በተከታታይ የሚሰጥ መሆኑን አቶ በላይ አሳውቀዋል።
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.