
የሕወት ክህሎት ማሰልጠኛ ማንዋልን ለማበልጸግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
የሕወት ክህሎት ማሰልጠኛ ማንዋልን ለማበልጸግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
ታህሳስ 22 ቀን 2017ዓ.ም ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር ተጠቃሚዎች ከመደበኛ የስልጠና ክፍለ ግዜያቸው ጎን ለጎን የህይወት ክህሎት ስልጠና የሚያገኙበት እድል ለማመቻቸት በተዘጋጀው ማንዋል አውደ ጥናት ተካሄደ።
በስፖርት ጤናማ፣ ንቁና አምራች ማኅበረሰብ ለመገንባት ከዮኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ያስታወሱት የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ዳይሮክቶሬት አቶ ጎሳዬ አለማየሁ የታዳጊ ወጣቶች ስልጠና ልማት መርሃ ግብር ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች በአረታች መሆናቸው ገልጸዋል፡፡
ላለፋት አንድ አመት እድሜያቸው ከ 10 -12 እንዲሁም ከ 13- 14 እድሜ ክልል ላሉ ሰልጣኞች ማስተማሪያ የሚውል የማሰልጠኛ ማንዋል እየተዘጋጀ መቆየቱን ያወሱት አቶ ጎሳዬ ማነዋል መነሻ በማድረግ ተከታታይ የአሰልጣኝነት ስልጠና ወሰዱ የተለያዩ ዲስፕሊን አሰልጣኞች በክረምት የስፖርት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሲሰሩበት መቆየቱን ተናግረዋል።
በአሰልጣኝነት ስልጠና የወሰዱ አሰልጣኞች በማንዋል ዝግጅት ትግበራ ወቅት ያጋጠሙ አንኳር ነጥቦች ተሰብስቦ ማንዋሉን ለማጠናቀቅ ታሳቢ ያደረገ አውደጥናት የተካሄደ ሲሆን መድረክ የተነሱ ሀሳቦች በማካተት ወደ ህትመት እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ አሰልጣኞች ኤክስፐርቶች የሚንስተር መስሪያቤት ተወካዮች መገኘታቸው ተመልክቷል፡፡
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎች ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን
ፌስ ቡክ ገጽ:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100069054105219
ቴሌግራም ቻናል: https://t.me/youthsport2014
ትዊተር
https://twitter.com/compose/tweet
ቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZM2j4H9mE/
ኢንስታግራም
https://www.instagram.com/addis_abeba_youth_and_sport_/
ኢሜል
addissport2013@gmail.com
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.